• Re-Invitation
  • Addis Ababa

Addis Zemen(Nov 28, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

በድጋሚ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የጉምሩክ ኮሚሽን አዲስ አበባ ኤርፓርት ጉምሩክ //ቤት በታክስ ዕዳ የያዘውን መኖሪያ ቤት ለመሸጥ ለሦስተኛ ጊዜ የወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

/ቤት ቁጥር 03/2018/

//ቤቱ ስማድል ኮሚውኒኬሽን ተርሚናል ፋብሪካ /የተ/የግ/ማህበር ለአለበት ዕዳ በታክስ ህጉ በተፈቀደው የጊዜ ገደብ ባለመክፈላቸው ምክንያት በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀጽ 41 በተሠጠው ስልጣን መሰረት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ /ከተማ ወረዳ 05 መገናኛ አከባቢ አምቼ ፊት ለፊት ለዋና አስፓልት መንገድ በጣም ቅርብ በሆነ ቦታ አክሰስ ሪል እስቴት እና እሳት አደጋ መከላከያ መካከል የሚገኝ የይዞታ ልዩ መለያ ቁጥር AA000060502305 የሆነ G+4 መኖሪያ ቤት ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም፡

1. በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራቾች ማንነቱን የሚገልፅ የነዋሪነት መታወቂያ (ፓስፖርት) ኮፒ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።

2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ እና ቅዳሜ ጠዋት 200_600 ሰዓት በአዲስ አዲስ አበባ ኤርፓርት ጉምሩክ //ቤት ገርጂ ጉምሩከ መጋዘን አስተዳደር ቅጥር ግቢ የዕቃ አወጋገድ ቡድን ቢሮ መውሰድ ይኖርበታል።

3. በግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ቤት የሰጡትን ዋጋ 1/10ኛውን ብቻ ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) በጉምሩክ ኮሚሽን አ/አ ኤርፖርት ጉምሩክ //ቤት (Customs COMMISSION ADDIS ABABA AIRPORT CUSTOMS BRANCH OFFICE ስም በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች በሚከተለው ጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት ሰነድ ገዝተው መጫረት ይችላሉ።

ተ.ቁ

የመ/ቤቱ ስም

ለጨረታ የቀረበው የንብረት አይነት

የንብረቱ መመልከቻ ቀን

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀን

1

አዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 የይዞታ ልዩ መለያ ቁጥር AA000060502305 የሆነ መኖሪያ ቤት

ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 30 ቀናት

ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 30 ቀን ከተጠናቀቀ በኃላ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን 800 ተዘግቶ በዚያኑ ቀን 815 ሰዓት ይከፈታል።

5. የጨረታ መክፈቻ ቦታ፡ገርጂ ጉምሩከ መጋዘን አስተዳደር ቅጥር ግቢ የጨረታ አዳራሽ የሰራተኞች ካፌ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።

6. በግልፅ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ ማስታወቂያው በጋዜጣ ወጥቶ 30 ቀን ከተጠናቀቀ በኃላ ቀጥሎ ባለው የስራ ቀን የመ/ቤቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የግልፅ ጨረታው መክፈቻና መዝጊያ ቀን ይሆናል።

7. የጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያስያዙት (CPO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር እንደ አስፈላጊነቱ የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የግልጽ ጨረታ ኮሚቴው መረጃውን አጣርቶ እንደጨረሰ 5 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

8. የቤት ጨረታ ለሚያሸንፉ ተጫራቾች ከስመ ንብረት ዝውውር ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ወጪዎች ሻጭን አይመለከትም።

9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ /ቤቱ በሚሰጠው አድራሻ ገቢ በማድረግ ያሸነፉበትን ሃብት ንብረት መረከብ ይኖርባቸዋል።

10. ከላይ በተ/ 9 በተገለጽት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ በማድረግ ንብረታቸውን ያልተረከቡ ተጫራቾች የግልፅ ጨራታው ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ (CPO) ያስያዙት የዋስትና ገንዘብ ለቅ//ቤቱ ገቢ ሆኖ ንብረቱ እንዳልተሸጠ ተቆጥሮ በቀጣይ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

11. //ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ የግልፅ ጨረታን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ///////ቤት

በስልክ ቁጥር 011 668 4537 እና 011 668 4193 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

በጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ኤርፓርት ጉምሩክ //ቤት