Addis Zemen(Nov 28, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር፡ ትሎሕዙ ብግጨ 001/2018
ኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ እህል፤ የጥራጥሬና የቅባት እህል፤ ሸቀጣሸቀጥ፣ ዘይት፣ ስኳር፣ ቡና እና አትክልትና ፍራፍሬ ምርቶች ግዥ በትራንስፖርት ዘርፍ የተሰማሩ አቅራቢዎችን በጨረታ በማወዳደር ግዥውን መፈጸም ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታ ላይ መወዳደር የሚፈልጉ
ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው፡፡
- የሚፈልገው የተሸከርከሪ ዓይነት
- ከጅቡቲ ለሚጓዙ ምርቶች (ዘይትና ስኳር) ደረጃ 1ና 2 ድንበር ተሻጋሪ የማጓጓዝ ፍቃድ ያላቸው
- በሀገር ውስጥ ለሚጓጓዙ የሀገር ውስጥ የማጓጓዝ ፍቃድ ያላቸው ደረጃ 4 እና ከዛ በላይ
- የመነሻ እና መዳረሻ ቦታ በጨረታ ሰነድ በተገለፀው መሰረት ይሆናል።
- ተጫራቾች በዘርፉ ለ2017/ 2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ጨረታው እስከሚከፈትበት ቀን ድረስ ሊያገለግል የሚችል የንግድ ሥራ ፈቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ሰርቲፊኬት፣ ከትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫም ሰርቲፊኬት፣ በጨረታ ለማሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ ክሊራንስ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት (TIN No) ይኖርባቸዋል። እነዚህ ሰነዶች በቴክኒካል ፕሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ታሽገው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከላይ የተገለጹትን ሰነዶች ከጨረታ ሰነድ ማቅረቢያው ቀን ገደብ በፊት ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 700.00 (ሰባት መቶ ብር) በመክፈል ከህዳር 22/2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡30 6፡30 ሰዓት እንዲሁም ከሰአት ከ7፡30- 11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 ሰዓት ድረስ ሁብት አስተዳደርና ግዥ ዋና ክፍል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከ ጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ ታህሳስ 08 /2018 ከጠዋቱ 4፡30 ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 50,000.00 አምሳ ሺህ ብር/ በሲፒአ ጥሬ ገንዘብ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ ኢንሹራንስ፤ ቦንድና ቼክ ተቀባይነት የላቸውም። የጨረታ ማስከበሪያው በቴክኒካል ፕሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ወይም ለብቻው ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል።
- የቴከኒክሰነድእናየፋይናንሻል ሰነድ በፖስታ በማሸግናኮፒእና ኦሪጅናል የፋይናንሻል እንዲሁምየቴክኒካል ሰነድ ኮፒዎችን ለየብቻ በፖስታ በማሸግ በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ ሁሉንም ፖስታዎች በማድረግ ታህሳስ 08 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የትራንስፖርትና ሎጀስቲከስ አገልግሎት ዘርፍ ዋናው መ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ አድራሻ ከታች ተገልጿል።
- አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ መጠን ለአሸነፉበት ጠቅላላ ዋጋ 10 ፐርሰንት በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ዘርፍ ስም አሰርተው ውሉን የሚፈጽሙ ይሆናል።
- ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር 251-11 437 9205 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ
አድራሻ፡–ቃሊቲ መንገድ ቆርኪ ፋብሪካ ፊት ለፊት አገልግሎት
ኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት