Addis Zemen (May 14, 2026)

አማራ ክልል

በአፈ/ከሳሽ ገብረሔር ኢንዱስትሪና አገልግሎት አክሲዮን ማህበር እና በአፈ/ተከሳሽ አሰፋ ዳኘው መካከል ስላለው የአፈፃፀም ክርክር ጉዳይ የአፈ/ተካሳሽ ንብረት የሆነውን ሲሚንቶ ብዛቱ 7281(ሰባት ሺህ ሁለት መቶ ሰማኒያ አንድ) ኩንታል ሲሚንቶ በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ሐበሻ ሲሚንቶ ፋብሪካ ግቢ ውስጥ የሚገኝ የአንድ ሲሚንቶ ዋጋ 1500.06 /አንድ ሺህ አምስት መቶ ብር ከዜሮ ስድስት ሳንቲም/ የሁሉም ብር ብዛት በጨረታ መነሻ ዋጋ 10,921,936.86 / አስር ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃያ አንድ ሺህ ዘጠኝ መቶ ሰላሳ ስድስት ብር ከሰማኒያ ስድስት ሳንቲም/ ሆኖ ግንቦት 06 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለ15 ቀን ያክል አየር ላይ እንዲውል ተደርጎ ጨረታው ግንቦት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ጨረታው የሚከናወን መሆኑን የደ ወሎ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት አዟል።

ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች በጨረታው ዕለት ስትመጡ 2% በፍ/ቤቱ ሀራጅ ባይ አካውንት 1000171246915 የሡፍ ሀሰን ማስያዝ ይኖርባችኋል።

የደ/ወሎ ዞን ከፍ/ፍ/ቤት