Addis Lessan(Nov 22, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።  

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 003/2018

በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ አስተዳደር ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ስራዎች ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን በማሟላት የሚሰሩ ስራ ተቋራጮች ማህበራት በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

ሎት

የስራው መጠሪያ

ወረዳ

የሚጋብዘው የስራ ተቋራጭ ደረጃ

የፕሮጀክቱ መጠናቀቂያ ጊዜ

የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና

1

አለም ብርሀን ቅድመ መደበኛ ት/ቤት አጥር እና ጥበቃ ቤት

1

በጥቃቅን አነስተኛ የተደራጁ ማህበራት ሆነው በአነስተኛ መብቃት እና በሽግግር ሂደት ላይ ያሉ ማህበራት (ይህንንም ካደራጃቸው ተቋም በኃላፊ የተረጋገጠ ማረጋገጫ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ብቻ)

 

30

ከተደራጁበት ወረዳ ዋስትና ደብዳቤ

2

አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ ቅድመ መደበኛ ትቤት አጥር አና ጥበቃ ቤት

12

3

ገላን ጤና ጣቢያ አጥር እና ጥበቃ ቤት

12

4

አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ ቅድመ መደበኛ ት/ቤት መፀዳጃ ቤት

12

5

ሳሪስ ጤና ጣቢያ መፀዳጃ ቤት፣ የእንግዴ ልጂ ቅበሪያ እና ቆሻሻ ማቃጠያ ቤት ስራ

6

6

ወረዳ 5 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት የወንዳች መፀዳጃ ቤት ግንባታ

5

7

ወረዳ 5 የመጀመረያ ደረጃ ትቤት የሴቶች መፀዳጃ ት/ቤት ግንባታ

5

 1. 2018 በጀት ዓመት የሚያገለግል የእድገት ደረጃ፣ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ ዓመታዊ ኦዲት ያስደረገ እና የገቢዎች ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል እንዲሁም ከተደራጁበት ወረዳ መደራጀታቸውን እና የተጠቀሱት መረጃው ትክክል መሆኑን የሚገልጽ ከወረዳው ደብዳቤ ማቅረብ የሚችል ኢነተርፕራይዝ

2. የዘመኑ የታደሰ ሰራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ

3. የግብር መለያ ቁጥር TIN NO ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

4. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5. የሲኦሲ COC ምዘና ማረጋገጫ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. በዲግሪ ተመርቀው በትምህርት ማስረጃቸው የተደራጁ ማህበራት የሲኦሲ (COC) የሙያ ብቃት ማረጋገጫ አይጠየቁም

7. የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል

8. መስሪያ ቤቱ ወቅታዊ ዋጋን አላገናዘቡም ብሎ ላመነባቸው የነጠላ ስራ ዋጋወች ወቅታዊ የዋጋ ስሌት (Cost Break Down) ማቅረብ የሚችሉ (የተጠየቀውን ወቅታዊ ዋጋ ስሌት (Cost Break Down) ማቅረብ የማይችሉ ተሳታፊዎች የጨረታ ሰነዳቸው ውድቅ ይደረጋል።

9. ተጫራቾች ለስራ ዝርዝሮቹ ያቀረቡት ዋጋ ወቅታዊ ዋጋን ያላገናዘበ ከሆነ ተጫራቹን ከጨረታው ያሰርዛል

10. ተጫራቾች ከተደራጁበት ከከተማ የስራና ከህሎት ጽ/ቤት የተሰጣቸውን የደረጃ እድገት ኮፒና ኦርጂናል ማቅረብ አለባቸው

11. ተጫራቾች በጨረታው ላይ ለመሳተፍ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማም ሆነ በተደራጁበት ክ/ከተማ ውስጥ በእጃቸው ላይ ስራ አለመኖሩን እና ስራም ካላቸው ከ70% በላይ ማጠናቀቃቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ከክ/ከተማው ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል

12. አሸናፊ ማህበራት ከተደራጁበት የስራና ክህሎት ጽ/ቤት ለቅድመ ክፍያ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው

13. ተጫራቾች በአንድ ቀን የጋዜጣ ማስታወቂያ ላይ ለወጡ የተለያዩ የክ/ከተማው ስራዎች አንድ ማህበር መሳተፍ የሚችለው በአንድ ጨረታ ላይ ብቻ መሆኑን አውቀው የሚወዳደሩበትን ጨረታ መምረጥ ይኖርባቸዋል። ከአንድ ጨረታ በላይ ወስደው የተገኙ ተጫራቾች ከውድድር ውጪ ይደረጋሉ።

14. የጨረታ ሰነዱን ከአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት 2ተኛ ፎቅ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ እስከ 21ኛው ተከታታይ ቀን ከላይ የተዘረዘሩትን ዋናና ኮፒ በመያዝ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

15. ተጫራቾች የወሰዱትን የጨረታ ሰነድ ሙሉ በሙሉ ሳይገነጣጠል ተመላሽ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል። ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሰነድ ተቀባይነት የለውም። የተሞላው የጨረታ ሰነድ አንድ ዋና እና ሁለት ኮፒ (እያንዳንዳቸው የታሸጉ እና በእያንዳንዳቸው ውስጥ የንግድ ፈቃድና የቫት ሰርተፊኬት ኮፒ የተካተተባቸው እና በእያንዳዱ ገፅ ማህተም የተመታበት) በማድረ ሁሉንም ሰነዶች በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ 7ኛ ፎቅ አዳራሽ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ እስከ ሃያ ሁለተኛው (22ተኛው) ቀን የጨረታ መመሪያው በሚያዘው መሰረት የጨረታ ሰነዱን ሁሉንም ሰነዶች በእንድ እናት ፖስታ በማሸግ እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ባለው ጊዜ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ኦርጅናሉ ላይ ኦርጅናል፣ ኮፒዎቹ ላይ ኮፒ በማለት መጻፍ ያለባቸው ሲሆን፣ ይህን አለማድረግ ከውድድር ያሰርዛል።

16. ጨረታው በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ 7ኛ ፎቅ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የፋይናንሻል ጨረታ ሰነድ ይከፈታል።

17. ተጫራቾች የሚቀጥሯቸው ሰራተኞች በርር ተመዝነው ሰርተፊኬት ያላቸው መሆን እና ያልተመዘኑም ከሆነ በCOC ለማስመዘን ዝግጁ እና ትብብር የሚያደርግ መሆን ይጠበቅበታል።

18. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

19. መስሪያ ቤቱ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሰነድ የማይቀበል መሆኑን እየገለጽን ስርዝ ድልዝ የተገኘበት ሰነድ ከጨረታው ውጪ የሚሆን መሆኑን እንገላጻለን።

20. የጨረታውን መመሪያ አለማክበር እና ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች አለማሟላት ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል።

አድራሻ ፡- ከቃሊቲ መናአሪያ ፊት ለፊት በሚገኘው አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ህንጻ ላይ ሁለተኛ ፎቅ የዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት የምህንድስና ግዢ ቡድን።

የአቃቂ ቃሊቲ ከፍለ ከተማ አስተዳደር ዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት