• Re-Invitation
  • Addis Ababa

Addis Zemen(Nov 24, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የተያዙና የተወረሱ ተሽከርካሪዎችንና ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ ማስታወቂያ

ቁጥር 25/2018

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ //ቤት የተተው፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ እንዲሁም ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን፣ የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፤ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) በግልጽ ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ተዘጋጅቶ ከሐሙስ ህዳር 18/2018 . ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑ እንገልጻለን፡፡

በመሆኑም፡

1. በተሽከርካሪ ግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ማንኛውም ዕድሜው 18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (C.P.O) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል፡፡

2. በዕቃ ግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (C.P.O) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኢንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ዉስጥ ማስገባት ይኖርበታል፡፡

3. በጨረታው ላይ የተሽከርካሪ ወይም የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሳተፍ አይችሉም።

4. ተጫራቾች የተሸከርካሪውንና የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ህዳር 18/2018 . ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በቅ//ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።

5.በዕቃና ተሸከርካሪ ግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸዉ ዕቃዎች ወይም ተሽከርካሪዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (C.P.O) በቅ//ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሠርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁሉ) መሰረት መጫረት ይችላሉ።

.

የቅ//ስም

የጨረታው አይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

. ቃሊቲ ጉምሩክ //ቤት

የእቃ ግልፅ

እስከ 23/03/2018

24/03/2018 345 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 400 ሠዓት ይከፈታል

የተሽከርካሪ ግልጽ

እስከ 23/03/2018

24/03/2018 345 ተዘግቶ በዚያውኑ ቀን 400 ሠዓት ይከፈታል

7. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡. ቃሊቲ ጉምሩክ //ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች /ሕጋዊ ወኪሎቻቸው/ ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።

8. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ 3 የሥራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል።

10. ከላይ በተ/ 9 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

11. /ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡ አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ -011-470-85-03

አድራሻ፡ ሳሪስ አቦ / በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ያለበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ

በጉምሩክ ኮሚሽን . ቃሊቲ ጉምሩክ //ቤት