West Wollega Zone Babo Gembel Woreda Finance Office
አዲስ ዘመን
(Aug 13, 2024)
የጨረታ ማስታወቂያ
በምዕራብ ወለጋ ዞን የባቦ ገምቤል ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዘመን ለወረዳው ለተለያዩ መሥሪያ ቤቶች
- የጽሕፈት መሣሪያዎች፣
- የሠራተኞች ደንብ ልብስ፣
- ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች፣
- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣
- የግንባታ ዕቃዎች፣
- ኤሌክትሮኒክሶች፣
- የጽዳት መሣሪያዎች፣
- ሕትመትና የሕትመት መሣሪያዎች፣
- የመኪና ጎማና ከመነዳሪ፣
- የሞተር ሳይክል ጎማና ከመነዳሪና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን
በዘርፉ ከተሰማሩ ተጫራቾች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተወዳዳሪዎች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው፤
- የዘመኑ የ2017 ግብር የከፈለና ፈቃዱን ያሳደሰ፤
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፤
- 7.5 ቫት እንሰበስባለን፤
- አሸናፊዎች ለሚያቀርቡት ዕቃ TOT (2%) የመክፈል ግዴታ አለባቸው፤
- በአቅራቢዎች መዝገብ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው፤
- ጨረታው የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በባቦ ገምቤል ገቢዎች ባለስልጣን ከፍለው ሰነዱን ከባቦ ገምቤል ወረዳ ገ/ጽ/ቤት መውሰድ የሚችሉ፡፡
- ተወዳዳሪዎች ለጨረታ ማስከበርያ 10,000 (አሥር ሺህ ብር) CPO ማስያዝ አለባቸው፡፡
- የጨረተው አሸናፊ ዕቃውን እስከ ባቦ ገምቤል ወረዳ ገ/ጽ/ቤት የዕቃ ግምጃ ቤት በጊዜው ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ፋይናንሺያልና የቴክኒክ ሰነድ ያለምንም ስርዝና ድልዝ ከሞላ በኋላ በተለያየ ፖስታ አሽጎ በኮፒና በኦሪጅናል ማቅረብ አለበት፡፡
- አሸናፊው ዕቃውን በጥራት ማቅረብ አለበት፡፡
- ካስፈለገ ናሙና ስንጠይቅ ማቅረብ አለበት፡፡
- የማይክሮ ኢንቴርፕራይዝ ተወዳዳሪዎች ለውድድሩ የሚረዳቸውን አስፈላጊ ዶክመንቶች ሁሉ ማስገባት አለባቸው፡፡
- የጨረታው ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ለ21 የሥራ ቀናት ከባቦ ገምቤል ወረደ ገ/ጽ/ቤት ማግኘት የምትችሉና በዚያው ቀን የጨረታው ማስገቢያ ሣጥን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተወዳዳሪዎችና ሕጋዊ ውክልና ባላቸው ፊት በይፋ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-057-1-17-00-05 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
በኦሮሚያ ብ/ክ/መንግስት በምዕራብ ወለጋ ዞን የባቦ ገምቤል
ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት