
Addis Ketema Sub City Felege Berhan Elementary School
አዲስ ዘመን
(Jan 31, 2025)
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 2/2017 ዓ.ም.
በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 የፈለገ ብርሃን የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በመደበኛ በጀትና ውስጥ ገቢ በጀት ሲፒኦ ከሚያሲዙ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የሎቱ አይነት |
ሎቱን የሚወክለው ዘርፍ |
ለየሎቱ የሚያዘው ማስከበሪያ ሲፒኦ መጠን |
ሎት 1 |
አላቂ የፅዳት እቃ |
3000 |
ሎት 2 |
የፕላንት ማሽነሪ እድሳት |
1000 |
ሎት 3 |
አላቂ የቢሮ ዕቃ |
1500 |
ሎት 4 |
ቋሚ ዕቃ |
3000 |
ሎት 5 |
አላቂ የትምህርት ዕቃ |
2000 |
ሎት 6 |
የሽልማት ዕቃ |
2500 |
ሎት 7 |
የተለያዩ የጥገና ስራ |
2000 |
ስለሆነ በጨረታ መሣተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባችዋል
- ተጫራቾች የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
- የ2016 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድና ክሪላንስ የታደሰ በተሰጣቸው ንግድ ዘርፍ ብቻ መሣተፍ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው
- ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጠቅላላ ብር 15,000.00 ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባችኋል።
- ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ ከት/ቤት ፋይናንስ ክፍል በግንባር ቀርበው ወይም ህጋዊ ወኪል አማካኝነት በብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር በመክፈል መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራቾች ላይ ተንተርሰው ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነዶችን ሞልተው በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ 11፡30 ማስገባት አለባቸው፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በእለቱ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ናሙና ያላቀረበ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይሆናል፡፡
- ውል ማስከበሪያ ስትዋዋሉ 10% እንድታይሲዙ
- ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመዘረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጥቃቅንና አነስተኛ ተወዳዳሪዎች በምታመርቱት ምርት ብቻ ነው መወዳደር የምትችሉት በተጨማሪም የጨረታ ሰነድ፣ ጨረታ ማስከበሪያ፣ ውል ማስከበሪያ ከአደራጃችሁ ተቋም አፅፋችሁ እንድታመጡ
- አቅራቢዎች ላሸነፋችሁበት እቃ በራሳችሁ ትራንስፖርት ት/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የገዙትን የግዥ ሰነድ በትክክል ሞልተውና ማህተማቸውን አድርገው መመለስ አለባቸው፡፡
አድራሻ – ጎጃም በረንዳ ከወለጋ ሆቴል ወደ ሩፋኤል በሚወስደው መንገድ ላይ ጨው በረንዳ ፊትለፊት ካለው አዲስ ህንፃ ወደ ውስጥ በግምት 50 ሜትር ገባ ብሎ
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር 011-2-73-32-42
በአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ በአዲስ ከተማ ክፍለ
ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የፈለገ ብርሃን
የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት