
Development Bank of Ethiopia
ሪፖርተር
(Jan 22, 2025)
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በዋና መ/ቤት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል መጋረጃ በጨረታ መለያ ቁጥር DBE/NCB/CU/001/2024/25 በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ተጫራቾች ከጨረታው መልስ ጋር የሚከተሉትን ተጨማሪ ሰነዶችን ያቀርባሉ፡
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ
- የግብር ከፋይ መለያቁጥር /TIN/
- የግብር ግዴታ ለመወጣቱ ከሀገር ውስጥ ገቢ
- ባለሥልጣን ወይም ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት የተሰጠ ተጫራቹ የግብር ግዴታ የተወጣ በመሆኑ ጨረታ ላይ መሳተፍ እንደሚችል የሚገልጽ የጽሁፍ ማስረጃ (ጊዜውያላላፈበትመሆንይኖርበታል)
- የተ.እ.ታክስ VAT/ ሰርተፊኬት
- የመንግስት ግዢ እና ንብረት አስተዳደተር የአቃራቢዎች ምዝገባ ሰርተፊኬት
- የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈጸም ቃል የሚገባበት ፎርማት ተሞልቶ የተጫራቹ ድርጅት ፊርማና ማህተም የተደረገበት
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 30,000 (ሰላሳ ሺህ) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች የዕቃዎቹን ዝርዝር/ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ/ ታወር ሁለት በባንኩ እግረኛ መግቢያ ክፍያውን ፈጽመው በባንኩ ታወር ሶስት 1ኛ ፎቅ ከግዥ ቡድን ቢሮ መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነድ ለተጫራቾች መሸጥ የሚጀምረው ጨረታ አየር ላይ ከጥር 14 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ነው።
- ተጫራቾች ጥያቄ ካላቸው ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ባሉት ተከታታይ አምስት ቀናት ውስጥ ማሳወቅ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከጨረታ መክፈቻ ሰአት በፊት ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ጨረታው መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በባንኩ ታወር ሶስት ህንጻ ላይ 1ኛ ፍሎር ግዥ ክፍል ኦሪጂናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ላይ ታሽጎ ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡05 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ባንኩ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ 0115-57-80-88 መደወል ይቻላል።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ