ANRS Building Construction Works Enterprise
አዲስ ዘመን
(Jan 08, 2025)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ስሕሥኮድ–ማሽግ/07/2017
የአማራ ሕንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት
- የተለያዩ የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎች እና ተከሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ አቅራቢዎችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ድርጅቱ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል።
- በዘርፉ የተሰማሩና በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ስራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN ያላቸው፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ቢሮ/ባህር ዳር አባይ ማዶ ኮበል ፊት ለፊት ባለው አስፓልት 300ሜትር ገባ ብሎ ካለው የአህስኮድ ዋና ቢሮ ወይም አዲስ አበባ የድርጅታችን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ከሚገኝበት ለገሃር አመልድ ህንፃ ሰባተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 02(ስልክ ቁጥር om265652)ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20(ሀያ) ተከታታይ ቀናት መግዛት ይችላሉ፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚያቀርቡት ማሽን(ተሽከርካሪ) ለእያንዳንዱ ሎት ጠቅላላ ዋጋ ቫትን ጨምሮ 2% ተቀባይነት ባላቸው ባንኮች በተረጋገጠ ትዕዛዝ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) Amhara Building Works Construction Enterprise በሚል ስም ተዘጋጅቶ መቅረብ አለበት፡፡ ተጫራቾች የቴክኒክ እና ፋይናንሻል የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሁለት በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች አንድ ቴክኒካል እና አንድ ፋይናንሻል ኦርጅናል በተጨማሪ አንድ ቅጅ ቴክኒካል እና አንድ ቅጅ ፋይናንሻል ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በአማራ ሕንጻ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት የማሽተሽ ግዥና አቅ/ኬዝ ቲም ቢሮ (ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበብ ህንጻ ፊት ለፊት የቀድሞው የአማራ ከተሞች ልማት ግንባታ አማ ግቢ) የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20ኛው ቀን (20 ተከታታይ ቀናትን በመቁጠር ) ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ብቻ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 20ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጀቱ የማሽተሽ/ግዥና ቢሮ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ20ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ታሽጎ በዛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል። 20 ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ታሽጎ በዛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ተከፍቶ ውድድሩ በዚሁ ዕለት የሚካሄድ ይሆናል።
- የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈባቸውን ማሽነሪዎች ባህርዳር አህስኮድ ዋና ቢሮ ድረስ በማምጣት የሚያስረክብ ይሆናል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ፡ ቁጥር፡ 058-320-5185/09 18 784 490/09 18 715 64 ወይም በፋክስ ቁጥር 058-218-0538
የአማራ ሕንጻ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት
ባህር ዳር