Federal Courts Judgment Execution Directorate

አዲስ ዘመን
(Jan 21, 2025)

የሐራጅ‍‌‌‌‍‍‍‍‌‍‌‌‍‌‍‍‌ ሽያጭ ማስታወቂያ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎

በፍ/ባለመብቶች እነ አቶ ፈለቀ ጌታሁን እና በፍ/ባለዕዳ ሙልየ ኩሸት መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር 160353 በ4/2/2016 ዓ.ም እና በመ/ቁ 165069 በ16/3/2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 4 የቤ.ቁ 304/10 የሆነ ቤት የፍ/ባለዕዳ ስም የተመዘገበ የቦታ ስፋት 54.15 ካ.ሜ ቤት የሐራጅ ሽያጭ መነሻ ዋጋ ብር 1,926,929 (አንድ ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሃያ ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ሃያ ዘጠኝ ብር) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ የካቲት 14 ቀን 2017 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል። የተጫራቾች ምዝገባ በ5፡00 ሰዓት‍‌‌‌‍‍‍‍‌‍‌‌‍‌‍‍‌ ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ው የሚካሄድ ይሆናል።

የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ በ3፡30 ሰዓት ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጎብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ው አይካፈልም። በጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ውን ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ዳ/ ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት። የፍ/አፈ/ዳይሬክቶሬት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።

በፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት