Butajera Town Correctional Facility
አዲስ ዘመን
(Jan 06, 2025)
የጨረታ ማስታወቂያ
የቡታጅራ ከተማ ማረሚያ ተቋም በህግ ጥላ ስር ለሚገኙ የህግ ታራሚዎች ከጥር 2017 ዓ/ም እስከ ሰኔ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ለ6 ወር ለምግብ አገልግሎት የሚውል፣
- ሎት 1. እህሎች፣
- ሎት 2 ማጣፈጫዎች ፣
- ሎት 3 የማገዶ እንጨት፣
- ሎት 4 የጽዳት እቃና የጽሕፈት መሣሪያ የዘመኑን የስራ ግብር የከፈሉ ተጫራቾች እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ የ2017 ዓ.ም ፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ቢሮ ተመዝጋቢ የሆኑ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ያላቸው የማይመለስ ብር 50 (ሃምሳ ብር) ብቻ ከፍለው የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታተታይ የስራ ቀናት ከማረሚያ ቤቱ ግ/ፋ/ን አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 06 መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእህል 10,000 ብር፤ ለማጣፈጫ 5,000 ብር ለማገዶ እንጨት 5,000 ብር፣ ለጽዳት እቃ 5,000 ብር፣, ለጽሕፈት መሣሪያ 10,000 ብር በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ጋር በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚከፈተው በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በ4፡30 ሰዓት ላይ በቡታጅራ ከተማ ማረሚያ ተቋም ግ/ፋ/ን/አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 06 ይከፈታል። ባይገኙም ከመከፈት አይታገዱም።
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት በራሳቸው ትራንስፖርት ቡታጅራ ማረሚያ ተቋም ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው።
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሰራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ለማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- የውል ማስከበሪያ ማስያዝ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች ለእህሉ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የቫት ተመዝጋቢ ከሆኑ ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ።
ለበለጠ መረጃ፡– 046-1-15-10-51/046-1-15-09-03
የቡታጅራ ከተማ ማረሚያ ተቋም