Abay Bank S.C.
አዲስ ዘመን
(Jan 06, 2025)
ያገለገሉ የተለያዩ የሆቴል እቃዎች
ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር፡– AB/PPM/05/15/2024-25
ዓባይ ባንከ አ.ማ በጎንደር ከተማ የባንኩ ንብረት በሆነው ቋራ ሆቴል ውስጥ አገልግሎት ሲሰጡ የቆዩ የተለያዩ ዓይነት የሆቴል መገልገያ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱትን የሆቴል እቃ ዓይነትና ዝርዝር ሁኔታ በጨረታው ሰነድ ላይ የሚገኝ ሲሆን የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በዓባይ ባንክ ቅርንጫፍ በመክፈልና ደረሰኙን በመያዝ ባምቢስ ኖክ ማደያ ፊት ለፊት በሚገኘው ዝቋላ ኮምፕሌክስ 8ኛ ፎቅ ከግዥና ንብረት አስተዳደር ዲፓርትመንት ወይም ጎንደር ከተማ በሚገኘው ዓባይ ባንክ ጎንደር ዲስትሪክት ቢሮ ከሰኞ ታህሳስ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 12 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ዘወትር በስራ ስዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 – 6፡00፣ ከሰዓት በኋላ ከ7፡00-11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት ማግኘት ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነድ የገዙ ተጫራቾች እቃዎችን ማየት ከፈለጉ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00–6፡00 ሰዓት ብቻ ጨረታው ከሚዘጋበት ቀን በፊት ጎንደር ከተማ ቀበሌ 03 ቋራ ሆቴል በአካል በመገኘት መመልከት ይቻላል።
- ተጫራቾች ከቀረቡት የጨረታ ሎት ውስጥ ሁሉንም ወይም የፈለጉትን ሎት መርጠው መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ሆኖም በአንድ ሎት ውስጥ ያሉትን እቃዎች መርጦ መግዛት አይችሉም።
- ተጫራቾች የሚጫረቱትን የሆቴል እቃዎች ዓይነት ዋጋ በትክክል ሞልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከታህሳስ 28 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ጥር 12 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡30 ሰዓት ድረስ በባንኩ ዋናው መ/ቤት ባምቢስ ኖክ ማደያ ፊት ለፊት ዝቋላ ኮምፕሌክስ 8ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዲፓርትመንት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ሰኞ ጥር 12 ቀን 2017 ዓ.ም 8፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት በ9፡00 ሰዓት በተጫራቾች ወይም ተወካዮች በተገኙበት በባንኩ ዋና መ/ቤት ዝቋላ ኮምፕሌክስ ህንጻ 3ኛ ፎቅ ግዥና ንብረት አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) በማሰራት ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚጫረቱትን ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) 15% ጨምሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 011-5-57-17-60/ 16-14 በመደወል መጠየቅ ይችላሉ።
ዓባይ ባንክ አ.ማ