Nebar General Trading Share Company
አዲስ ዘመን
(Jan 07, 2025)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ነባር አጠቃላይ ንግድ አክሲዮን ማህበር በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ክልል በሚገኘው የአክሲዮን ማህበሩ ንብረት በሆነው ሕንፃ ላይ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ ጉዳት የደረሰበትን የጉዳት መጠን (Damage Assessment) ማሰራት ስለሚፈልግ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን የሃገር ውስጥ እና አለም አቀፍ ተጫራቾች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
በመሆኑም የሚከተሉትን መስፈርቶች አሟልተው መወዳደር የሚችሉ ተጫራቾችን ይጋብዛል::
1. በዘርፉ ለመሰማራት የሚያስችል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል (ከብሔራዊ ባንክ) ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤
2. በሲቪል ምህንድስና የማማከር ፈቃድ እና የሙያ ብቃት ያላቸው፤
3. የዘመኑን የታደሠ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው፤
4. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
6. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤
8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በሂሳብ ቁጥር 1000184750507 ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን የባንክ የገቢ ደረሰኝ በመያዝ ነባር አጠቃላይ ንግድ አክሲዮን ማህበር ሕንፃ ላይ 1ኛ ፎቅ በሚገኝው ጊዜያዊ ቢሮ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ። በተጨማሪ የተቃጠለውን ህንፃ ጉብኝት /Site Visit/ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
9. ተጫራቾች የጨረታ ውድድሩ ቴክኒካል እና ፋይናንሺያል ግምገማ ስለሚኖረው ቴክኒካል አንድ ኦሪጂናል አንድ ኮፒ እና ፋይናንሺያል አንድ ኦርጂናል አንድ ኮፒ በማሸግ በድምሩ አራት ሰነድ ለየብቻው በታሸገ ፖስታ የድርጅቱን ፊርማ፣ ማህተም እና የሚወዳደሩበትን የስራ ዓይነት ስም በመፃፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትናም (BID BOND) ለብቻ በታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱን ፊርማ እና ማህተም በማድረግ ማስገባት ይኖርባችኋል:: በተጨማሪም የታሸገውን 3 ፖስታ የፋይናንሻል ሰነድ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ እንዲሁም ሦስቱን ፖስታ (የፋይናንሻል፣ የቴከኒካል እና የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና) በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተም፣ፊርማ እና የሚወዳደሩበትን የስራ አይነት በመፃፍ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል።
10. ጨረታው ሕጋዊ ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጥር 12 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ከልል በሚገኘው ወረዳ 01 ነባር አጠቃላይ ንግድ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
አክሲዮን ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-09-11-24-63-12 ወይም 09-45-98-68-45 መደወል ትችላላችሁ።
ነባር አጠቃላይ ንግድ አክሲዮን ማህበር