Semada Woreda Finance and Economic Development Office
በኩር
(Jan 06, 2025)
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ጎንደር አስተዳደር ዞን የስማዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስተዳደር ቡድን በ2017 በጀት ዓመት ለስማዳ ወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚዉሉ በመደበኛ በጀት በካልም በጀት፣ በሪድ ፕላስ በጀት
- ሎት 1. የጽህፈት መሳሪያ፣
- ሎት 2. የግንባታ እቃዎች፣
- ሎት 3. ኤሌክትሮኒክስ፣
- ሎት 4. የውሃ እቃ፣
- ሎት 5 የጽዳት ዕቃ፣
- ሎት 6 የመኪና እና የሞተር ጎማ፣
- ሎት 7 የተዘጋጀ ፈርኒቸር፣
- ሎት 8 የስፖርት ዕቃ፣
- ሎት 9 ብሎኬት፣
- ሎት 10 የተዘጋጁ ልብሶች፣
- ሎት 11 የሙጌ አሸዋ፣
- ሎት 12 የተከሰከሰ ጠጠር እና
- ሎት 13 ጥቁር ድንጋይ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ተጫራቾች ማሟላት የሚፈለግባቸው መስፈርቶች፡-
1. ህጋዊ ወቅታዊ የታደሰ በዘርፉ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የዘመኑን ግብር የከፈሉና ቲን ካርድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
3. ተጫራቾች የሞሉት ዋጋ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውንና ሌሎች መረጃዎቻቸውን በፖስታ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በስማዳ ወረዳ ግ/ን/አስ/ደ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 26 ለሥራው በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
5. ጨረታው በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ይከፈታል፡፡
6. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሃብ ስማቸውን ፣ፊርማቸውን ማህተማቸዉንና ሙሉ አድራሻቸውን ማስፈር አለባቸው፡፡
7. የጨረታው ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሀሣብ ላይ ለውጥ ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው እራሣቸውን ማግለል አይችሉም ሥርዝ ድል ፍፁም
የተከለከለ ነዉ፡፡
8. ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደሚሆኑና ለወደፊቱም በመንግስት የግዥ ጨረታ እንዳይሳተፉ የሚደረጉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
9. ተጫራቾች ለሥራው የተዘጋጀውን ሠነድ የማይመለስ 50.00 /አምሳ ብር/ ብቻ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ስ/ወ/ገ/ያዥ ቢሮ ቁጥር 12 መግዛት ይችላሉ፡፡
10. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ አንድ በመቶ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ለዋና ገንዘብ ያዥ ማስያዝና ያስያዙበትን ኮፒ ፖስታ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
11. ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ አስር በመቶ የውል ማስከበሪያ በጥሬ ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ /ሲፒኦ/ ማቅረብና ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
13. ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው ቢገኙም ባይገኙም ይከፈታል፡፡
14. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
ለበለጠ ማብራሪያ በሥልክ ቁጥር 058 667 01 67 ደውሎ ወይም ግ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 26 በአካል ጠይቆ መረዳት ይቻላል፡፡
የስማዳ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት