Addis Zemen (May 23, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢመአ/ሻሽ/094/2018
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ለ2018 በጀት ዓመት ለዲስትሪክቱ የመንገድ ጥገናና ግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የተለያየ መጠን ያላቸው የተፈጩ ጠጠሮችን በግልጽጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሠረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠብቅባቸዋል፡፡
1. ተጫራቾች የ2018 ዓ.ም የታደሰ ንግድ ፍቃድ የምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርቲፍኬት እና የግብር ከፋይ ምስክር ወረቀት ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
2. ተጫራቾች ለ2017 በጀት ዓመት ግብር ስለመከፈላቸው የሚገልጽ ክሊራንስ ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።
4. ተጫራቾች ዋጋ የተሞላበትን ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በማድረግ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በእለቱ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
5. ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከሰዓት በኃላ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ የሚከፈት ይሆናል። በእለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
6.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1000002579859 ገቢ በማድረግ የገቢ ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ ከሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት ዕቃ ግዥ/አ/ን/አስተዳደር ቢሮ የጨረታ ሰነዱ መግዛት ይቻላል።
7. በጨረታው መክፈቻ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም መስሪያ ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው።
8 ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0462-114-616 መጠቀም ይችላሉ።
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር
የሻሸመኔ መንገድ ጥገና ዲስትሪክት
{ document.querySelectorAll(selector).forEach(el => { if (el.closest('#job-detail-content')) { el.style.display = 'none'; } }); }); // Also hide the action buttons const actions = document.querySelector('.job-actions'); if (actions) actions.style.display = 'none'; // Restore after printing (attach listener BEFORE calling print) window.addEventListener('afterprint', function restore() { selectorsToHide.forEach(selector => { document.querySelectorAll(selector).forEach(el => { el.style.display = ''; }); }); if (actions) actions.style.display = ''; window.removeEventListener('afterprint', restore); }, { once: true }); // Now trigger the print dialog window.print(); } function downloadJobPDF() { printJobDetails(); }