Addis Zemen (May 09, 2026)

የማሽን ኪራይ ጨረታ ማስታወቂያ

በጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት /ቤት 2018 በጀት ዓመት በዛይሴ ኤልጎ ማዘጋጃ ቤት በጫሞ ዳር 01 ቀበሌ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ጠረጋና ጠጠር የማልበስ ስራ የተለያዩ ማሽኖች ኪራይ በግልጽ ጨረታ በደቡብ ንጋት ጋዜጣ ማስታወቂያ በማሳወጅ ለመከራየት ይፈልጋል። በዚሁ መሠረት በጨረታው መሳተፍ የሚችሉት በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችና ግለሰቦች ሲሆኑ ለጨረታው ውድድር ማቅረብ ያለባቸው መስፈርት በክልሉ ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ የተመዘገቡና የብቃት ማረጋገጫቸዉን ያሳደሱ የታደሴ ንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸውየአቅራቢነት ሰርተፍከት፤ የተጨማሪ ስእሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍከት የግብርመክፈያ መለያ ቁጥር 2017 በጀት ዓመት ግብር የከፈሉበት ክሊራንስ እንዲሁም የማሽኖች መረጃ የራስ ከሆነ የባለቤትነት ደብተር /ሊብሬ/ ለማገናዘብ ኦርጅናልና ኮፒ የኪራይ ከሆነ ወቅታዊና በሕግ አካል የፀደቀ የኪራይ ውል ለማገናዘብ ኦርጅናልና ኮፒ የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም ከታወቀ ባንክ የባንክ ክፍያ ማዘዣ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ከታወቀ ባንክ ቢድ ቦንድ እና መልካም ስራ አፈፃፀም ቢያንስ ሁለት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አባሪ አድርገው ማቅረብ አለባቸው።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ/ በመክፈል ከመ/ቤቱ ግዥና ንብረት አስተዳዳር መወሰድ ይችላሉ። ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ነጠላ ዋጋ ከመሙላታቸው አስቀድመው የስራ ሳይቱን በራሳቸው ወጪ ተንቀሳቅሰው ማየት አለባቸው ስለማየታቸው ማረጋገጫ ደብዳቤ ከአሰሪው ማዘጋጃ ቤት ማቅረብ ይገባቸዋል።

ሁሉም ተጫራች የግንባታ ማሽኖችን በራሱ ወጭ በሎቤድ ጭኖ አስገብቶ የሚሰራ መሆኑን ማወቅ አለበት።

ተጫራቾች የፋይናንሻል ጨረታ ሰነድ ያለ ስርዝ ድልዝ በጥንቃቄ በመሙላት በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ማህተምና ፊርማ በማኖር አንድ ኦርጅናልና 2 ኮፒ በማዘጋጀት ኦርጅና ኮፒ 1 ኮፒ 2 በማለት ለየብቻው በፖስታ በማሸግ በእናት ፖስታ አጠቃሎ በማሸግ እንዲሁም ቴክኒካል ሰነድንም በተመሳሳይ በማዘጋጀት በፖስታው ላይ የጨረታው ዓይነት የተጫራች ስልክ በመጻፍ በዕለቱ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤ የጨረታ ማስከበሪያ ቴክኒካል ኦርጅናል ውስጥ ተካቶ መታሸግ አለበት። በሌላ በኩል የአርትሜቲክ ስህተት ካስነበበው ዋጋ 3% በላይ እንዲሁም ያቀረበው ዋጋ ከመሀኒዲስ ግምት 5% በላይና 25% በታች ቅናሽ ከዐ% በላይ ሲሆን ተጫራቹ ከጨረታ ውጪ ይሆናል።

ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 500 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ በዕለቱ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ይከፈታል። 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ሂደቱ ይከናወናል። ሰዓቱ በአግባቡ ይድረስ እንጂ ተጫራቾች መገኘት አለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም።

/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር 046-181-409-1-09-832-6-1648

በጋሞ ዞን የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት /ቤት