Addis Zemen(Jan 19, 2026)

የጉምሩክ ኮሚሽን . ቃሊቲ ጉምሩክ //ቤት

የተያዙና የተወረሱ ተሽከርካሪዎችንና ልዩ ልዩ ዕቃዎች

ሽያጭ ማስታወቂያ ቁጥር 36/2018

በአዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ //ቤት የተተዉ፣ የተወረሱ እና በኮንትሮባንድ ተይዘው የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን በግልጽ ጨረታ እንዲሁም ንብረቶችን (የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን፣ሞባይሎች፣ የሞባይል ክፍሎች፣ የኤሌከትሮኒክስ እቃዎችን፣ የቤትና የቢሮ ዕቃዎችን የተለያዩ የተዘጋጁ አልባሳትና ጫማዎች፣ የውበት መጠበቂያ ዕቃዎች እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎችን) በግልፅና በሐራጅ ባሉበት ሁኔታ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ከዚህ በታች በቅፁ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ለጨረታ የሚቀርቡ ንብረቶች ዝርዝር መረጃ ተዘጋጅቶ ከሀሙስ ጥር 14/2018 . ጀምሮ ለተጫራቾች በሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ላይ የሚታወቅ መሆኑ እንገልጻለን።

በመሆኑም

1. በተሽከርካሪ ግልጽ ጨረታ ለመሣተፍ ማንኛውም ዕድሜው 18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ በማስገባት በጨረታው ሊሳተፍ ይችላል።

2.በዕቃግልጽ ጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በዘርፉ የፀና የንግድ ፍቃድ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ሰነዶች ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ ወይም (CPO) ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ ወይም በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የሚኖርበት ሲሆን ለሃራጅ ጨረታ ደግሞ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ይዞ ማስመዝገብ ይኖርበታል።

3. በጨረታው ላይ የተሽከርካሪ ወይም የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰቡ የነበሩ ሰዎች መሣተፍ አይችሉም።

4. ተጫራቾች የተሽከርካሪውንና የዕቃዎቹን ጨረታ ሰነድ ከሀሙስ ጥር 14/2018 . ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በመክፈል በቅ//ቤቱ በመገኘት የጨረታ ሠነዱን መግዛት ይችላሉ።

5. በዕቃና ተሽከርካሪ ግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች ወይም ተሽከርካሪዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ለጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በቅ//ቤቱ አድራሻ ስም CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA KALITY CUSTOMS BRANCH OFFICE በባንክ አሰርተው ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

6. የዕቃ ሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ለዕቃዎች ብር 100,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) በተ. 5 በተገለጸው አድራሻ ተጫራቹ ማስያዝ አለበት፡፡ ነገር ግን በዕቃ ሐራጅ በጨረታ ሰነድ ላይ በሚገለጹ የተወሰኑ ዕቃዎች ላይ የጨረታ ማስከበሪያ ቼክ (CPO) መጠን የሚወሰን መሆኑን እንገልጻለን።

7. ተጫራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (ስኬጁል) መሰረት መጫረት ይችላሉ።

.

የቅ//ቤቱ ስም

የጨረታው ዓይነት

የንብረት መመልከቻ ቀን የጨረታ ሰነድ ከወሰዱ ቀን ጀምሮ

የጨረታው የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

1

. ቃሊቲ ጉምሩክ //ቤት

የእቃ ሐራጅ

እስከ 18/05/2018

19/05/2018 400 ሠዓት ጀምሮ ይካሄዳል፡፡

የእቃ ሐራጅ

እስከ 19/05/2018

20/05/2018 345 ተዘግቶ በዚያው ቀን 400 ሠዓት ይከፈታል

የተሽከርካሪ ግልጽ

እስከ 19/05/2018

20/05/2018 345 ተዘግቶ በዚያው ቀን 400 ሠዓት ይከፈታል

8. የጨረታው መክፈቻ ቦታ፡. ቃሊቲ ጉምሩክ //ቤት የሚካሄድ ሲሆን ጨረታው ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።

9. ተሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት (CPO) የጨረታው ውጤት በተገለፀ 3 የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

10. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ 5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሣት ይኖርባቸዋል።

11. ከላይ በተ/ 10 በተገለፁት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

12. /ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡አዲስ አበባ ቃሊቲ ጉምሩክ 011 – 470 – 85 03

አድራሻ፡ሳሪስ አቦ / በቀለበት መንገድ ወደ ማሰልጠኛ በሚወስደው መንገድ ኖክ ማደያ ያለበት አዲሱ ህንጻ ገንዘብ ያዥ ቢሮ አዲስ ህንፃ ገንዘብ ያዥ ቢሮ

የጉምሩክ ኮሚሽን . ቃሊቲ ጉምሩክ //ቤት