
Kaffa Zone Gimbo Woreda Agriculture, Environment Protection & Cooperative Work Office
አዲስ ዘመን
(Dec 17, 2024)
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር-6
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት በካፋ ዞን ጊምቦ ወረዳ ግብርና አከባቢ ጥበቃ እና ህብረት ሥራ ጽ/ቤት በ2017 ዓ/ም በFOLUR ፕሮጀክት በአማራጭ ሀይል አቅርቦት ላይ በዋናነት ምርጥና ትክክል / mirt stove used for boiling And Tikikil stove used for boiling/ ማገዶ ቆጣቢ ምድጃን ለተጋ ቀበሌ ፣ለበየሞ ቀበሌ ፣ለጋዋ ቀበሌ፣ ለያበክቻ ቀበሌ እና ለባቃ ቀበሌ ወይም ለ5 ፕሮጀክት ቀበሌዎች የ1.7 ሚልዮን ብር የሚያወጣ ምድጃ ከአቅራብ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ ከህጋዊ ተጫራቾች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡-
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያለውና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያላቸውና በመንግሥት ግዥ እንድሳተፉ የሚዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
- የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000 /ሠላሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል። የጨረታውን ሠነድ ከጊምቦ ወረዳ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 14 ቀርበው የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ /ብር በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች በጨረታ ሠነዱ ላይ በተጠየቀው መጠይቅ መሠረት ብቻ ዋጋውን በመሙላትና በመፈረም ህጋዊ የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍና በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው ለ15/ አሥራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ16ተኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ሲሆን ታሽጎ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ባይገኙም የጨረታውን መክፈት አያስተጓጉልም፡፡
- በጨረታ ከፈታ ወቅት የምገኝ ተወካይ ከተወከለበት ድርጅት ኦርጅናል የውክልና ደብዳቤ ይዞ የመገኘት ግዴታ አለበት።
ጨረታውን ያሸነፍ ተጫራች እስከ ጊምቦ ወረዳ ግብርና ልማት ጽ/ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት። - የጨረታ አሸናፍ ድርጅት ጨረታውን ማሸነፉ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት ውስጥ ቀርቦ ከገዥ መ/ቤት ጋር ውል ገብቶ የውሉን አጠቃላይ ግንዘብ በጊምቦ ወረዳ ፋይ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት በተከፈተው ትሬዥሪ አካውንት 1000198892697 ላይ ገቢ በማድረግ ውል መፈፀም አለበት፡፡
ጨረታው የሚታሸግበት ቅዳሜ፣እሁድ ወይም ከስራ ቀን ውጭ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀንና በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል::
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፍልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ስበስጠ መረጃ በስልክ ቀጥር፡- 047 222 6490/055 ይደውሉ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት በካፋ ዞን ጊምቦ
ወረዳ ግብርና አከባቢ ጥበቃ እና ህብረት ሥራ ጽ/ቤት