
Refugee and Returnee Service
አዲስ ዘመን
(Aug 10, 2024)
ጨረታ ማስታወቂያ
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት ለሰራተኞች የደንብ ልብስ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ተጫራቾች –
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በጨረታ ለመወዳደር የሚያስችል ክሊራንስ፣ ሕጋዊና የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ እና በጨረታ ለመሳተፍ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያሳይ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው።
- የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ወይም ሂሣብ ክፍል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ቅዳሜና እሁድ የመስሪያ ቤቱ የስራ ቀናት አይደሉም፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የሥራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዳቸውን በአገልግሎት ዋና መ/ቤቱ የግዢ ቡድን ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 እንዲሁም ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 11፡00 ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ተጨማሪ እሴትታክስን ጨምሮ የሚያቀርቡትን አጠቃላይ ዋጋ 2% ለስደተኞችና ተመላሾች Refugees and Returnees Service በሚል የተዘጋጀ የባንክ የክፍያ ማዘዣ /CPO ወይም የባንክ ዋስትና (Bank Guarantee) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- አገልግሎት መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት
ምስኪ ህንፃ
ከዋሽንግተን የህክምና ማዕከል 500 ሜትር እንደተጓዙ
ወደ ቦሌ ሚካኤል በሚወስደው መንገድ ከታክሲ ተራው በቀኝ በኩል
አዲስ አበባ
ለተጨማሪ ማብራሪያ፤
በስልክ ቁጥር፡- 011 813 21 93 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የስደተኞችና ተመላሾች አገልግሎት አዲስ አበባ