Addis Zemen (Jul 13, 2026)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
በፍርድ ባለመብት አየለ ፍስሀ እና በፍርድ ባለእዳ አማኑኤል ገ/ጻድቅ መካከል ስላለው አፈፃፀም የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመ/ቁ 17761 በቀን 22/9/2017 ዓ.ም በኮ/መ/ቁ.19156 በቀን 29/11/2017ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትእዛዝ በአልፋቤት ት/ቤት ኃ/የተ/የግ/ማህበር በአቶ አማኑኤል ገ/ጻድቅ ያለቸው የአክሲዮን ብዛት 500 (አምስት መቶ) የአንድ አክሲዮን ዋጋ 1000 (አንድ ሺህ) አጠቃላይ የአክሲዮን ዋጋ 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) የሽያጭ ዋጋ መነሻ ግምት ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ሆኖ የትራንዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ነሐሴ 7 ቀን 2018 ዓ.ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትናባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን፤እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል። ከ1/4ኛው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም። በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ/ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251112730852 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የፌዴራል ፍ/ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት
{ document.querySelectorAll(selector).forEach(el => { if (el.closest('#job-detail-content')) { el.style.display = 'none'; } }); }); // Also hide the action buttons const actions = document.querySelector('.job-actions'); if (actions) actions.style.display = 'none'; // Restore after printing (attach listener BEFORE calling print) window.addEventListener('afterprint', function restore() { selectorsToHide.forEach(selector => { document.querySelectorAll(selector).forEach(el => { el.style.display = ''; }); }); if (actions) actions.style.display = ''; window.removeEventListener('afterprint', restore); }, { once: true }); // Now trigger the print dialog window.print(); } function downloadJobPDF() { printJobDetails(); }