Addis Zemen (Mar 31, 2026)

በድጋሚ አየር ላይ የዋለ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ጨ.ፌ.መ.ህ.ግ. ፕ.ጽ/ቤት02/2ዐ18

በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የፌዴራል መንግስት ህንጻዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ የግንባታ እቃዎችን በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡

  • ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋጋ ሞልተው ሲመልሱ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  • ተጫራቾች ከጨረታው ቀን በፊት ንብረቶቹ በአራት ኪሎ በሚገኘው የግንባታ ሳይት ላይ በሚገኙበት ቦታ ቀርበው ማየት ይችላሉ።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያውን ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በአንድ ላይ በማጠቃለል አስተማማኝ በሆነ ማጣበቂያ በታሸገ ፖስታ በማድረግ የተወዳዳሪ ስምና አድራሻ በመጻፍ ማህተም ወይም ፊርማ በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ሶስት መቶ (300) ብር በመክፈል ከፌዴራል መንግስት ህንጻዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ግዥና ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በስራ ሰዓት ፕሮጀከት ጽ/ቤቱ ግዥና ንብረት ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  • ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 8፡30 ሰዓት ላይ በግዥና ንብረት ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ የመክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል፡፡ ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ ጨረታው በሚከፈትበት ሰዓት ባይገኙ የጨረታው መከፈት የማያስተጓጉል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታው ሂደት ለተላላፈ ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  • ተጫራቾች የሚፈልጉትን እቃ ብቻ መጫረት የሚችሉ ሲሆን ከመነሻ ዋጋ በታች መጫረት አይቻልም፡፡
  • ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርጉ ተጫራቾች ጨረታው ተሰርዞ የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
  • አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉትን ዕቃ በራሳቸው የማጓጓዣ ወጪ አራት ኪሎ በሚገኘው የጠቅላይ ፍርድ ቤት የህንጻ ግንባታ ሳይት ውስጥ ከሚገኙ መጋዘኖች ወጪ በማድረግ በ5 ቀናት ውስጥ መውሰድ ይኖረበታል፡፡
  • ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  • የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ – ቦሌ መንገድ ሀንሰም ህንጻ ላይ 5ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 502

ስልክ ቁጥር፡- 011 5 58 12 28

በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የፌዴራል መንግሥት ሕንፃዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት

{ document.querySelectorAll(selector).forEach(el => { if (el.closest('#job-detail-content')) { el.style.display = 'none'; } }); }); // Also hide the action buttons const actions = document.querySelector('.job-actions'); if (actions) actions.style.display = 'none'; // Restore after printing (attach listener BEFORE calling print) window.addEventListener('afterprint', function restore() { selectorsToHide.forEach(selector => { document.querySelectorAll(selector).forEach(el => { el.style.display = ''; }); }); if (actions) actions.style.display = ''; window.removeEventListener('afterprint', restore); }, { once: true }); // Now trigger the print dialog window.print(); } function downloadJobPDF() { printJobDetails(); }