Addis Zemen (Feb 27, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ/ክ/መ/በወላይታ ዞን የድጉና ፋንጎ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ልማት ጽ/ቤት ከወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት ጋር በመሆን በ2018 በጀት ዓመት በዋን ዋሽ ናሽናል ፕሮግራም በተላከው በጀት በጤና ኬላዎች ባለ ሁለት ክፍል መፀዳጃ ቤት፣ 10000 ሊትር ሮቶ ከነማስቀመጫ እና የደረቅ ቆሻሻ መጣያ ጉድጓድ ግንባታ ሥራዎች በድጋሚ በግልጽ ጨረታ ሕጋዊ ተወዳዳረዎች አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል።

ሎት 1፤ በጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት በፋንጎ ኦፋ ጤና ኬላ ላይ ባለ ሁለት ክፍል ሽንት ቤት ግንባታ እና በፋንጎ ዳሞታ ጤና ኬላ ላይ ደረቅ ቆሻሻ መጣያ ግንባታ ሥራዎች

ሎት 2፤ በጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት በድጉና ኦፋ፤ ፋንጎ ሁምቦ እና ቢላቴ ጨርቾ ጤና ኬላ ላይ ደረቅ ቆሻሻ መጣያ እና በፋንጎ ቢጆ ጤና ኬላ ደረቅ ቆሻሻ እና 10,000ሊትር ሮቶ ከነማስቀመጫ ግንባታ ሥራዎች

በዚህ መሠረት መጫረት የምትችሉ ተጫራቾች ፡-

1. የ2018 ዓ.ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱ፤ /ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ፤ ቲን መለያ ቁጥር ያላቸው፤ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፤ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸውና በፌዴራል ግዥና የመንግሥት ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢነት ምዘገባ/በበይነ መረብ የተመዘገበን ማቅረብ የሚችሉ እና ደረጃ BC/GC-6 እና ከዛ በላይ ያላቸው።

2. 3% ለመንግሥት ግብር እንደሚቆረጥ ማወቅ አለባቸው።

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 200.00 (ሁለት መቶ) ብር በመክፈል ከወ/ዞ/ድ/ፋ/ወ/ፋኢል/ጽ/ቤት የንግድ ፍቃዳቸውን ዋናውን በመያዝ ከቢሮ ቁጥር 13 መግዛት ይችላሉ፤

4. ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸውን ቴክኒካል ግምገማ መስፈርቱን ከዋናው ሰነድ ማግኘት ይችላሉ፤ (የጨረታው ሰነድ ከጨረታ ማስታወቂያ ጋር እኩል ዋጋ ይኖረዋል)፤

5. ተጫራቾች በአሁኑ ሰዓት ያላጠናቀቁና በውል ያላስረከቡ ፕሮጀክት በእጃቸው ካለ ጨረታውን መወዳደር ብቁ አይደሉም ወይም ከጨረታው ውድቅ ይሆናሉ፤(ተጫራቾች ፕሮጀክቱን ያጠናቀቁበትን የመልካም ሥራ አፈጻጸም

6. እያንዳንዱ ዶክመንት በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልተው ቴክኒካል እና ፋይናንሻል አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ሁሉንም ለየብቻቸው ታሽገው እና የጨረታ ማስከበሪያውን በተለየ ፖስታ ለብቻው በማቅረብ ሁሉም ዶክመንት በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ በሰም አሽገው ማድረግ ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ/ cpo/ካሽ/ ብር 15,000 (አስራ አምስት ሺህ) ጨረታው ከተከፈተ ለ60 ቀናት የሚቆይ ማቅረብ ይኖርባችኋል።

8. ተጫራቾች የመስክ ምልከታ ድጋፍ ከወረዳው ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት መቀበል ይኖርባችኋል።

9. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመስረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ የማይነበብና ስርዝ ድልዝ ያለው መሆን የለባቸውም።

11. ስለዚህ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ በ30 /ሰላሳ/ ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ከሰዓት ጀምሮ እስከ 30ኛው ቀን የሚቆይ ሲሆን ከላይ የተገለፀውን መሥፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች የሚያቀርቡበትን ዋጋ በመግለጽ ፖስታውን በሰም አሽገው ዘወትር በሥራ ሰዓት ድ/ፋ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስተዳደር ዋና የሥራ ሂደት ጨረታ ክፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማኖር ይችላሉ።

12. ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበትም ባልተገኙበትም በ31ኛው የሥራ ቀን ልክ ከጠዋቱ 4፡30 ሲሆን የፖስታ ሳጥን በ4:00 ጠዋት ታሽጎ በ4:30 ጠዋት ይከፈታል ዕለቱ በዓል እና ሰንበት ከሆነ በሚቀጥለው ሥራ ቀን ይሆናል።

13. የሂሳብ ማስተካከያ ስህተት ከ3% በላይና በታች መሆን የለበትም

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር /09 16 71 99 03/ 09 16 11 42 41/ 09 16 00 32 50/

በወላይታ ዞን የድጉና ፋንጎ ወረዳ ፋይናንስ ፕላን ልማት ጽ/ቤት /ቢጠና/

{ document.querySelectorAll(selector).forEach(el => { if (el.closest('#job-detail-content')) { el.style.display = 'none'; } }); }); // Also hide the action buttons const actions = document.querySelector('.job-actions'); if (actions) actions.style.display = 'none'; // Restore after printing (attach listener BEFORE calling print) window.addEventListener('afterprint', function restore() { selectorsToHide.forEach(selector => { document.querySelectorAll(selector).forEach(el => { el.style.display = ''; }); }); if (actions) actions.style.display = ''; window.removeEventListener('afterprint', restore); }, { once: true }); // Now trigger the print dialog window.print(); } function downloadJobPDF() { printJobDetails(); }