Addis Zemen (Mar 08, 2025)
የጨረታ ማስታወቂያ
አዲስፋ/ግጨ/045/2017
በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ (አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ) ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን የጥበቃ ሠራተኞች ጫማ እና ደንብ ልብስ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1፡ የጥበቃ ሠራተኞች የስራ ጫማ
- ሎት 2፡ የጥበቃ ሠራተኞች የስራ ደንብ ልብስ (ሽሮ መልክ)
ስለሆነም በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላችሁ አካላት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን የምታሟሉ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ድረስ ለገሀር አሮጌ ባቡር ጣቢያ ወደ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን 4ኛ ክፍለ ጦር አካባቢ አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቀርበው ለዚህ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
- የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ክፍያ መለያ ቁጥር (Tin. No) ያላቸው፤ በሚወዳደሩበት ዘርፍ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም በመንግስት መ/ቤት ግዢ ለመወዳደር እንደሚችሉ ከገቢ ሰብሳቢ ድርጅቶች ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ላይ የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ማቅረብ የሚችሉ።
- የሚጫረቱበትን ዋጋ በእያንዳንዱ በጨረታ ሰነድ መሠረት እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በሁለት የታሸገ ፖስታ መቅረብ ያለበት ሲሆን በቴክኒካል ፖስታ አስፈላጊ ሰነዶች ትክክለኛ ኮፒ እና የጨረታ ማስከበሪያ አብሮ መቅረብ አለበት።
- ናሙና ማቅረብ ይኖርበታል።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ሊገኙ ፈቃደኛ በሆኑ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪላቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ነገሮች ማሻሻል ወይም መተው አይችልም።
- የጨረታው ተሳታፊዎች (አቅራቢዎች) ከዚህ በላይ የተገለጹትን በአግባቡ ሳይፈጽሙ ቢቀሩ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለፋብሪካው ገቢ ሆኖ ተጫራቹ ከጨረታው ይሰረዛል።
- ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት ከዚህ በታች በተገለጸው አድራሻ አዲስ አበባ ለገሀር አሮጌ ባቡር ጣቢያ ወደ ቂርቆስ ቤተክርስቲያን 4ኛ ክፍለ ጦር አካባቢ አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ስልክ 0910147760/0912 102754 በመደወል ወይም ዘወትር በስራ ሰዓት በግንባር በመቅረብ ማነጋገር ይቻላል፡፡ ፋብሪካው ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ አርጆ ዲዴሳ ስኳር ፋብሪካ