Addis Zemen (Mar 07, 2025)
በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክ/መ/ባህል ቱሪዝም ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ለሙዚቃ የሚውሉ ዕቃዎችን ግዥ በጨረታ ኣወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ተ.ቁ | የዕቃው ዓይነት | የጨረታ ማስከበሪያ Bid Bond/CPO/ |
1 | የሙዚቃ መሣሪያ | 10,000 |
2 | ካዝና | 1,000 |
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የታደሰ የሥራ ፍቃድና የዘመኑን የሥራ ግብር አጠናቀው የከፈሉበት ማስረጃ የአቅራቢነት የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ፣ የንግድ መለያ ቁጥር ጨምሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ለ15 የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ባህል ቱሪዝም ቢሮ በአካል በመምጣት ወይም በተወካይ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ብር 100 /አንድ መቶ/ በመክፈል ሰነድ መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድና ሌሎች ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕና የጨረታውን ስምና ቁጥር በመጥቀስ ከ28/6/2017 ዓ.ም እስከ 18/7/2017 ዓ.ም 11፡30 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ መጨመር ይኖርባቸዋል፡፡
4. ጨረታውን በ19/7/2017 ዓ.ም በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮሌጁ ይከፈታል።
5. ቢሮው የተሻለ ሁኔታ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
6. አሸናፊው ከተረጋገጠ በኋላ ወዲያውኑ ሌሎች ያስያዙት ዋስትና ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ይመለሳል።
7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሀሳብና ዋጋ ታክስን የሚያካትትና የማያካትት መሆኑን በትክክል መግለጽ አለበት፡፡
8. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ሀሳብና ዋጋ ላይ ፊርማቸውን፣ ቀንና የድርጅቱ ማህተም ማሳረፍ ይኖርባቸዋል፡፡
9. አሸናፊው ተጫራች አገልግሎቱን ሙሉ በሙሉ በውሉ መሰረት ማጠናቀቃቸው ከተረጋገጠ በኋላ ሙሉ ክፍያ ይከፈላቸዋል፡፡
10. የጨረታ መክፈቻው በበዓላትና በእረፍት ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀናቶች ላይ ይሆናል፡፡
11. የተጫራቾች ያለመገኘት የጨረታውን የመክፈት ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
12. በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
13. ተጫራቾች የሥራ ፍቃዳቸው ያልተሟላ መረጃና በሥራ ዝርዝሩ ሰነድ ላይ የሚሞሉት የነጠላ ዋጋ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፣ የመወዳደሪያ ዘዴ በዓይነት ይሆናል፤
14. በአነስተኛ ጥቃቅን አዋጅ መሰረት የተደራጁ ማህበራት ከአደራጁ መ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤና የቁጠባ ካፒታል ከባንክ ወይም፣ ከኦሞ ማይክሮ ፋይናንስ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
15. ጨረታውን ያሸነፈ አቅራቢ እስከ ማ/ኢ/ከ/መ/ሳጃ ባ/ቱ/ቢሮ ድረስ ዕቃውን ማቅረብ ይኖርበታል።
16. የመወዳደሪያ ቋንቋ በአማርኛ ሲሆን የግዥ ጠያቂ ቢሮ የሚፈልገውን ዝርዝር ዕቃ ሙሉ በሙሉ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፤
17. የሥራው ቦታ የም ዞን ሳጃ ከተማ ሲሆን ከአዲስ አበባ 240 ኪ.ሜ ወደ ጅማ በሚወስደው መንገድ ላይ ትገኛለች፤
18. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡– /09 19 10 82 88/09 12 99 92 06 ደውሎ ማግኘት ይችላሉ፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ባህልና ቱሪዝም ቢሮ