
Tebela City First Instance Court
የደቡብ ንጋት
(Jan 25, 2025)
በድጋሚ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ
በአፈጻጸም ከሳሽ ወ/ሮ ትግስት እማኑ እና በአፈጻጸም ተከሳሽ አቶ ጥላሁን ሚልኩ መካከል ባለው የአፈጻጸም ፍ/ር ክስ መ/ቁ 02279 የሆነው በወላይታ ዞን በጠበላ ከተማ አስ/ር 01/አላታ/ ቀበሌ ውስጥ በምስራቅ ሻ/ል ታከለ አለሙ፣ በሰሜን 10 ሜትር መንገድ፣ በደቡብ አቶ ነጻነት እስራኤል እና በምዕራብ 10 ሜትር መንገድ አዋስኖ የሚገኝ 300 ካ.ሜ የከተማ ይዞታና በላዩ ላይ ያለው 82(ሰማንያ ሁለት) 18 ቅጠል ቆርቆሮ ክዳን መኖሪያ ቤት፣ 18 ቅጠል ኩሽና ቤት መነሻ ዋጋ ግምት 814,554.8 (ስምንት መቶ አስራ አራት ሺህ አምስት መቶ ሀምሳ አራት ብር ከሰማንያ ሳንቲም/ ተገምቶ ለሃራጅ ሽያጭ በድጋሚ የወጣ ስለሆነ ለመጫረት ለመግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበትና የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታ መውጣቱን አውቆ መጫረት የሚችል ሆኖ ተጫራቹ ያሸነፈበትን 25 ፐርሰንት ለጨረታ አስፈጻሚ ባለሙያ በማስረከብ የሚችልና ቀሪውን 75 ፐርሰንት ደግሞ የግዥነት መብት ከታወቀበት ቀን ጀምሮ ባለው 15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ መክፈል የሚችል ተጫራች በቀን 24/06/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30-6፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ተገኝተው መጫረት የሚችሉ መሆኑን ፍ/ቤቱ አዟል፡፡
በደ/ኢ/ክ/መ/ወላይታ ዞን ጠበላ ከተማ መጀ/ደ/ፍ/ቤት