Addis Ababa City Administration Public Procurement and Property Disposal Service

አዲስ ዘመን
(Jan 25, 2025)

የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ ማስታወቂያ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተለያዩ ተቋማት የሆኑ ያገለገሉ የተለያዩ

  • ተሽከርካሪዎች፣ በስክራፕ መልክ የሚወገዱ የሸገር ዳቦ መሸጫ ባሶች፣ የባቡር ፋርጎ ብረቶች፣
  • ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ የተለያዩ መጠን ያላቸው ያገለገሉ የDCIቧንቧ ብረቶች፣ የብረት ቧንቧዎች፣
  • የአገልግሎት ዘመናቸውን የጨረሱ ተጠግነው አገልግሎት የማይሰጡ ኮምፒውተርና ተያያዥነት ያላቸው የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና
  • የተለያዩ ንብረቶች (የተሸከርካሪ ጎማዎች፣ ባትሪዎች፣ ከነመዳሪዎች፣ ቸርኬዎች፣ ፍላፖች፣ በርሜሎች እና
  • ያገለገሉ የህከምና መገልገያ ንብረቶች እና ሌሎችም) ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ ለመሸጥ ይፈልጋል፡
  1. ተጫራቾች ከአፍንጮ በር ወደ 6 ኪሎ በሚወስደው መንገድ ፍቅር ፕላዛ ህንፃ ላይ በሚገኘው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 306 በመምጣት የተለያዩ ተቋማት ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች፣ በስክራፕ መልክ የሚወገዱ የሸገር ዳቦ መሸጫ ባሶች ተሽከርካሪዎች፣ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ የባቡር ፋርጎ ብረቶች እና የተለያዩ መጠን ያላቸው ያገለገሉ DC ቧንቧዎች፣ የተለያዩ መጠን ያላቸው የብረት ቧንቧዎች ለእያንዳንዳቸው ዝርዝርና ብዛት የያዘ የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ ሰነድ የማይመለስ ብር 400.00 (አራት መቶ ብር)፣ እንዲሁም የአገልግሎት ዘመናቸውን የጨረሱ ተጠግነው አገልግሎት የማይሰጡ ኮምፒውተርና ተያያዥነት ያላቸው የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና የተለያዩ የአገለገሉ የንብረቶች (የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ባትሪዎች፣ ቸርኬዎች፣ ፍላፖች፣ ከነመዳሪዎች፣ በርሜሎች፣ የህክምና እቃዎች እና ሌሎችም) ዝርዝርና ብዛት የያዘ የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ማስታወቂያ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 የስራ ቀናት ቅዳሜን ጨምሮ ተገኝተው መግዛት ይችላሉ፡፡
  2. በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው አምድ ስር ዋጋ በአሃዝ እንዲሁም በፊደል ያለ ስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 402 ለዚሁ ሥራ በተዘጋጀው የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ው እስከ ሚታሸግበት ሰዓት‍‌‌‌‍‍‍‍‌‍‌‌‍‌‍‍‌ ድረስ ተጫራቾች ሰነድን ማስገባት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራቾች በአሃዝና በፊደል እንዲሁም በነጠላና በጥቅል በሰጡት ዋጋ መካከል ልዩነት ካለ አገልገሎቱ ከፍተኛውን ዋጋ ወስዶ ያወዳድራል፡፡
  4. ተጫራቾች ትክክለኛ አድራሻቸውንና ስማቸውን በመግለጽ በመጫረቻ ሠነዳቸው ላይ መፈረም አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቶች በአንድ መለያ ቁጥር(መደብ) ስር ያለውን ንብረት ብዛት በሙሉ መጫረት አለባቸው፡፡
  6. ተጫራቾች ለሸያጭ የተዘጋጁትን የተሽከርካሪ ጎማዎች፣ ቸርኬዎች፣ ባትሪዎች፣ ፍላፖች፣ ከነመዳሪዎች፣ በርሜሎች፤ የህከምና መገልገያ እቃዎች እና ሌሎችም የአንዱን መስሪያ ቤት በጥቅል መጫረት አለባቸው፡
  7. ተጫራቾች ንብረቱ በሚገኝበት ቦታ ድረስ በመሄድ ንብረቱን አይተው መጫረት ወይም ዋጋ መስጠት አለባቸው፡፡ነገር ግን ንብረቱን ሳያዩ ቢጫረቱና ቅሬታ ቢቀርብ አገልግሎቱ ሀላፊነቱን አይወስድም፡፡
  8. ለሚገዙት የተለያዩ ተቋማት ተሽከርካሪዎችና በቁርጥራጭ መልክ የሚወገዱ ተሸከርካሪዎች የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ መነሻ ዋጋውን 20 በመቶ (20%)፣ ሌሎችን ንብረቶችን፣ የባቡር ፎርጎ ብረትን ፣ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች እና የተለያዩ መጠን ያላቸው ያገለገሉ DCI ቧንቧዎች፣ የተለያዩ መጠን ያላቸው የብረት ቧንቧዎች ደግሞ የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ መነሻ ዋጋውን 10 በመቶ (10%) እንዲሁም የአገልግሎት ዘመናቸውን የጨረሱ ወይም ተጠግነው ዳግም አገልግሎት የማይሰጡ የኮምፒውተርና ተያያዥነት ያላቸው የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ስም አሰርተው ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ሳጥኑ ውስጥ ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ ማስከበሪያ ዋጋ ሲ.ፒ.ኦ. ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡
  9. የአገልግሎት ዘመናቸውን የጨረሱ ወይም ተጠግነው ዳግም አገልግሎት የማይሰጡ የኮምፒውተርና ተያያዥነት ያላቸው የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች አሸናፊ ተጫራች ክፍያውን በተመለከተ የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ አሸናፊው ከአገልግሎቱ ጋር በሚደረግ የውል ስምምነት መሰረት ይፈፀማል፡፡ሆኖም የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ አሸናፊው የውሉን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የሚያስይዙ ይሆናል፡፡
  10. የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ ሳጥን ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት መሰብሰቢያ አዳራሽ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 504 ይከፈታል፡፡ ሆኖም የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ መክፈቻ ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ሰዓት ይከፈታል፡፡ 
  11. ተጫራቾች በራሳቸው ምርጫ ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ በመቅረታቸው የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ውን አከፋፈት አያስተጓጉልም፡፡
  12. ተሽከርካሪዎች የነበረባቸው የቦሎ ዕዳ እና የስም ዝውውር ወጪ በአሸናፊ ተጫራቾች ይሸፈናል፡፡
  13. አንድ ተጫራች አንድ ተሽከርካሪ እና ከአንድ የመ/ቤት ንብረቶች በላይ መግዛት ይችላል፡፡ ሆኖም አንድ ተጫራች ለአንድ ተሽከርካሪ፤ ለአንድ መደብ ንብረት የተለያየ ዋጋ በመስጠት መወዳደር አይችልም፡፡
  14. በመነሻ ዋጋና በታች የቀረበ ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡
  15. የባቡር ፋርጎ አሸናፊ የሆነው ተጫራች ፋርጎዎችን ለመቆራሪጥም ሆነ ቆፍሮ ለማውጣት የሚወጡ ማንኛውም ወጭዎችን የሚሸፍን ይሆናል፡፡
  16. የDCI ቧንቧብረቶች እና የተለያዩ መጠን ያላቸው የብረት ቧንቧዎች አሸናፊ ተጫራች ብረቱን በራሱ ወጭ ቆራርጦ የሚወስድ ይሆናል፡፡
  17. የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ ሳጥን ከተዘጋ በኋላ ኮድ ወይም መለያ ቁጥር ሲጽፍ ተሳስቻለሁ ወይም ሳልጽፍ ቀርቻለሁ የሚሉ ጥያቄዎች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
  18. በጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ7 የስራ ቀናት ውስጥ ገንዘቡን መክፈል ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ ማስከበሪያ ለአገልግሎቱ ገቢ ይደረጋል፡፡
  19. ንብረቱን በ10 የስራ ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፡፡
  20. ማንኛውም ተጫራች በጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ ተካፋይ ሆኖ ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ው ከተዘጋ በኋላ ከጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ው መውጣት ወይም የሰጠውን ዋጋ ማሻሻል ወይም መለወጥ አይችልም፡፡
  21. የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጡ ማናቸውም ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈስገ በስልክ ቁጥር 011 -557-86-71 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት