Habesha Cement Share Company

ሪፖርተር
(Dec 29, 2024)

የተለያዩ የደህንነት መጠበቂያ መገልገያዎችን ለመግዛት የወጣ ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎

Procurement Ref. No. HCSC/EHS/001/2017

ድርጅታችን ሐበሻ ሲሚንቶ አክሲዮን ማህበር የተለያዩ የደህንነት መጠበቂያ መገልገያዎችን ሕጋዊ ፈቃድ ካላቸው አቅራቢዎች በጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሟሉ ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በፖስታ አሽገው ለሎጅስቲክስ እና ግዢ መምሪያ እስከ ጥር 02 ቀን 2017 . ከጠዋቱ 400 ሰዓት‍‌‌‌‍‍‍‍‌‍‌‌‍‌‍‍‌ ድረስ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ው በዕለቱ 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት መሆኑን እያሳወቅን ተወዳዳሪዎች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ከላይ እስከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ድረስ ብቻ ከታች በተመለከተው አድራሻ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

  1. ማንኛውም ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያለው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈለ ድርጅት በጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ው መወዳደር የሚችል ሲሆን ተጫራቾች የፈቃዳቸውን ኮፒ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆቸው ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር አብረው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች ለጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ ዋጋ የሚያቀርቡባቸውን እቃዎች መጥቀስ/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: በተጨማሪም ዋጋ ያቀረቡበትን የዕቃ አይነት በግልጽ መጻፍ ይኖርባቸዋል።
  3. ተጫራቾች የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ ማስከበሪያ ብር 150,000 (አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይንም የባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  4. ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ው ከተዘጋ በኋላ የሚቀርቡ የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ ሰነዶችም ሆኑ ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ው ከተከፈተ በኋላ የሚደረጉ የማሻሻያ ጥያቄዎች ተቀባይነት የላቸውም።
  5. አሸናፊ ሆኖ የተመረጠ ተጫራች አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ውል በመግባት 7 ባልበለጡ የሥራ ቀናት ውስጥ ዕቃዎቹን ማቅረብ ይጠበቅበታል።
  6. ተጫራቾች ያቀርቡት ዋጋ ከቫት ወይም ከማንኛውም የመንግስት ታክስ በፊት ወይም አጠቃላይ ዋጋ(ማለትም ቫት እና ሌሎች የመንግስት ታክስ ክፍያዎችን ያጠቃለለ) ስለመሆኑ በግልፅ ማመልከት ይኖርባቸዋል:: ይህ ባልሆነበት እና በግልፅ የማያቀርቡ ተጫራቾች ከጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ው ሊሰረዙ ይችላሉ:: ስርዝ ድልዝ የዋጋ ማቅረቢያ ተቀባይነት አይኖረውም።
  7. ተጫራቾች ለግዥ የቀረቡትን የደህንነት መጠበቂያ እቃዎች ዝርዝር እንዲሁም ተጨማሪ መረጃዎችን የያዘውን የመጫረቻ ሰነድ ከዚህ በታች በተቀመጠው የድርጅቱ አድራሻ ማግኘት ይችላሉ።
  8. ሐበሻ ሲሚንቶ ኢማ ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‏‎‎‏‎‏‏‎ውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን በተጨማሪም ለግዥ የቀረቡትን አቃዎች ዝርዝር ብዛት የመጨመርም የመቀነስም መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡ አሮጌው ቄራ ከንግድ ማተሚያ ቤት ጀርባ

ጌትአስ ኢንተርናሽናል ሕንፃ 7 ፎቅ

ስልክ፡ 0114 163 273/ 09 44 122 311/09 12 850 906

ሐበሻ ሲሚንቶ .