
South Water Works Construction Enterprise
አዲስ ዘመን
(Aug 16, 2024)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2016
የደቡብ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ያገለገሉ የተለያዩ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች፣ አዳዲስና ያገለገሉ የኮንስትራክሽን ግንባታ ዕቃዎች፣ አዳዲስና ያገለገሉ የተሽከርካሪና ማሽነሪ መለዋወጫዎችን፣ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን እና ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች (ተረፈ ምርቶችን) ተጫራቾች በተገኙበት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በድርጅቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለሽያጭ የተዘጋጁ የተለያዩ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ የጨረታ ሰነድ በመግዛት መመልከት ይችላል።
ሎት | የዕቃዎች ዝርዝር |
01 | ያገለገሉ የተለያዩ ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች |
02 | አዳዲስና ያገለገሉ የኮንስትራክሽን ግንባታ ዕቃዎች |
03 | አዳዲስና ያገለገሉ የተሽከርካሪና ማሽነሪ መለዋወጫዎች |
04 | ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች |
05 | ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች( ተረፈ ምርቶች) |
- ተጫራቾች ለጨረታ የተዘጋጀውን ሠነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ ከታች በተጠቀሰው የድርጅቱ ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ፤ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ /Bank slip/ ይዞ በመቅረብ ከብሎክ ቁጥር 9 ቢሮ ቁጥር 1 መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታው ሠነድ የሚሸጥበት ጊዜ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው ተከታታይ 15 /አስራ አምስት የሥራ ቀናት በስራ ሰዓት ይሆናል።
- ሠነዱን ለመግዛት የሚመጡ ተጫራቾች ማንነታቸውን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ በመያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ውክልና ያላቸው ንብረቶችን ማየት የሚችሉት ሠነዱን ከገዙ በኋላ የገዙትን ሠነድ ኦርጅናሉንና ማንነታቸውን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያቸውን በማሳየት ይሆናል። በተመሳሳይ መልኩ ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ውክልና ያላቸው ማንነታቸውን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ያልያዘ ወደ ጨረታ አዳራሽ መግባት አይችልም።
- የጨረታው ሰነድ 1 አንድ/ ኦሪጅናል እና ሀ/ አንድ/ ኮፒ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለየብቻ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። እንዲሁም ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 20% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል። ሠነዱ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 መግባት ይኖርበታል።
- በ16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ በድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኘው የሠራተኞች መሰብሰቢያ አዳራሽ ጨረታው የሚከፈት ይሆናል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚካሄድ ይሆናል።የተለየ ሁኔታ ካለ በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት በውስጥ ማስታወቂያ የምናሳውቅ ይሆናል።
- ተጫራቾች በጨረታ ሠነድ ላይ ከተዘረዘሩት ንብረቶች የፈለጉትን ያህል ለመግዛት መጫረት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሚጫረቱት ዝርዝር ዕቃዎች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን 20% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ለ60 /ስልሣ/ ቀን የሚቆይ ማስያዝ አለባቸው/
- ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ምንም ዓይነት የጨረታ ሠነድ ሽያጭ አይከናወንም።
- ጨረታውን ያሸነፈው አካል ከፍያውን የሚፈጽመው ለዚሁ ጉዳይ በተከፈተው በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የድርጅቱ ሂሳብ ቁጥር (1000013538542 ደቡብ ውሃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ኤች አይ ቪ) በማስገባት የባንክ ደረሰኝ (Bank slip) በማቅረብ ይሆናል።
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈበትን ገንዘብ ከላይ በተጠቀሰው በድርጅቱ ሂሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ ንብረቱን የማንሳት ግዴታ አለበት። ገንዘቡን ገቢ አድርጎ ንብረቱን በo (አሥር) ቀናት ውስጥ ያላነሳ ተጫራች ያስያዘው ሲፒኦ / CPO / 20% ውርስ ተደርጎ መግዛት ለሚፈልግ ለሌላ ተጫራች በአሸናፊው ዋጋ ድርጅቱ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ለመሸጥ ይችላል።
- ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፡_ 09 11 902 728/ 09 11 094 266/ 09 13 040 244
ሐዋሳ
ደቡብ ውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት