Practical Life Development Association
አዲስ ዘመን
(Jan 06, 2025)
የጨረታ ማስታወቂያ
ፒ.ኤል.ዲ አሶሴሽን (ፕራክቲካል ላይፍ ዴቨሎፕመንት አሶሴሽን) አምቦ ውስጥ ባሉ ወጣቶች የተቋቋመ ሀገር በቀል ለትርፍ ያልተቋቋመ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን በጥር 04 ቀን 2013 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በመዝገብ ቁጥር 5334 ተመዝግቦ ፈቃድ የተሰጠው ድርጅት ነው፡፡ ሆኖም ድርጅታችን የ2023 እና የ2024 እ.ኤ.አ የሂሳብ ሰነድ በጨረታ አወዳድሮ በውጪ አዲተር ማስመርመር ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም የስራ ዘርፉ የሚመለከታችሁ ተጫራቾች ፒ.ኤልዲ አሶሴሽን በ 2023 እና 2024 እ.ኤ.አ የስራ እንቅስቃሴ አጠቃላይ ሰነድ አንድ ቦክስ ፋይል መሆኑን እየገለጽን የድርጅቱ ስራ ቦታ አምቦ ሁለተኛ ደረጃ የመሰናዶ ትምህርት ቤት ወደ ወሊሶ መሄጃ መንገድ 300 ሜትር ገባ ብሎ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ የኦዲት አገልግሎት ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- የኢትዮጵያ ሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ መስሪያ ቤት የተመዘገቡ እና ህጋዊ የኦዲት ስራ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፤
- የግብር መክፈያ ቁጥር (TIN Number) ሰርተፊኬት የሚያቀርቡ
- በተመሳሳይ የስራ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ (NGO) ላይ 2 (ሁለት) እና ከዚያ በላይ የስራ ልምድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ ለሂሳብ ምርመራ አገልግሎት ለስራው ከሚጠይቁት ዋጋ ለጨረታ ማስከበሪያ 3% የተመሰከረለት ቼክ ወይም ጥሬ ገንዘብ የተከፈለበት ደረሰኝ የጨረታ ሰነድ ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራች ድርጅቱ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 5 የተዘረዘሩትን መረጃዎች እና ለስራው ያቀረበውን ዋጋ እንዲሁም ስራውን አጠናቆ የሚያስረክብበትን ጊዜ በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርጎ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጊዜ አንስቶ እስከ ጥር 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ድረስ በፒ.ኤልዲ አሶሴሽን ዋና ቢሮ አምቦ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ጥር 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 5፡30 ይከፈታል።
- ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በጨረታው አይገደድም
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0941 44 41 44/0921 91 70 36 በመደወል መረጃ ማግኘት ይቻላል፡፡
ፒ.ኤስ.ዲ አሶሴሽን (ፕራክቲካል ላይፍ
ዱበሎፕመንት አሶሴሽን)