
Chancho City Finance Office
አዲስ ዘመን
(Jan 23, 2025)
ለ2ኛ ግዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጫንጮ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 ዓ/ም የበጀት ዘመን ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች (ፈርኒቸር) በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፡-
- በጨረታው መካፈል የምትፈልጉ እና በተጠቀሰው የስራ መስኮች የተሰማራችሁ ነጋዴዎች በበጀት ዓመቱ የሚያገለግል የንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የቫት ተመዝጋቢ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ እና ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
- የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት እና ከግብር ነፃ መሆንን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ፤
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 10,000 (አስር ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ CPO በጫንጮ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት በሚል ስም በማሰራት ማቅረብ የሚችል፤
- ጨረታውን ያሸነፈ ተወዳዳሪ የክፍያ ሂሳብ 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) እና ከዛ በላይ ከሆነ With Holding Tax (7.5) መክፈል ይጠበቅበታል።
- የጨረታ ሰነዱን በስራ ሰዓት የማይመለስ 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ከጫንጮ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ በወጣ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 በጫንጮ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- ስልክ ቁጥር /0912 125 865/0923 105 546
በሰሜን ሸዋ ዞን የጫንጮ ከተማ ገንዘብ ጽ/ቤት
ጫንጮ