Central Ethiopia Regional Government Gurage Zone Finance Department
አዲስ ዘመን
(Jan 07, 2025)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-5-2017
የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለጉራጌ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ እያስተዳደረው ያለው የወልቂጤ እስታዲየም ውስን ስራዎች ጥገና ለማከናወን ተቋራጮችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች በማመልከቻ ሲጠይቁ ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡–
1. ህጋዊ ምዝገባ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤
2. በደረጃቸው ጂሲ-5 እና ከዚያ በላይ ደቃድ ያላቸው፤
3 የዘመኑን ንግድ ፈቃድ ያደሱ ሆነው ዋናውንና ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፤
4. የዘመኑ የኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
5. በጨረታ መወዳደር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት የጨረታ ሰነድ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መቅረብ አለባቸው።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በጉራጌ ዞን ገቢዎች በመክፈል ጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 18 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
7. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውን እና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
8. በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን እና ሌሎች ተፈላጊ መረጃዎችን ማለትም 1 ፋይናንሻል ኦሪጅናል እና 2 ኮፒ በጥንቃቄ በተናጠል በታሸገ ፖስታ 1 ቴክኒካል ኦርጅናል እና 2 ኮፒ በጥንቃቄ በተናጠል በታሸገ ፖስታ በመለያየት በጥንቃቄ በታሸገ እናት ፖስታ ከጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 18 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ የአካባቢ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 21 ቀናት ውስጥ ማስገባት ይጠበቅበታል፡፡
10. ከተራ ቁጥር 1-8 የተጠቀሱትን መስፈርቶች ሙሉ በሙሉ ያላሟሉ ተጫራቾች ከውድድር ውጪ ይሆናሉ፡፡
11. የጨረታ ማስከበሪያ ብር 150,000.00 /አንድ መቶ ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም የግዥ መምሪያ በሚፈቅደው ዋስትና ለ120 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ስም ተዘጋጅቶ ከሚያቀርቡት ኦሪጅናል ቴክኒካል ፕሮፖዛል ጋር በተናጠል ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
12. ጨረታው በ21ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ8፡30 ሰዓት ላይ በጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ አዳራሽ ውስጥ በይፋ ይከፈታል፡፡ ተቋራጮች (ወኪሎቻቸው) ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
13. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ /የህዝብ በዓል/ ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ ፡–
የጉራጌ ዞን ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ከሚከታተላቸው ፕሮጀክቶች ውስጥ በአፈጻጸማው ምክንያት 3 ዙር ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ውል ያቋረጡ ተጫራቾች መወዳደር አይችሉም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ሂደት ውስጥ ተሻሽሎ የወጣው የክልሉ መመሪያ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ለበለጠ መረጃ መ/ቤቱ ድረስ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 0113–30-01-12 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በማዕ/ኢት/ክ/መ/የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ