![South Wollo Zone Finance Command](https://diretenders.com/wp-content/plugins/wp-job-manager/assets/images/company.png)
South Wollo Zone Finance Command
አዲስ ዘመን
(Jan 08, 2025)
ሀገር አቀፍ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 6 ደወገመ/ግቡ/563/2017
የደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ አገልግሎት ከሚሰጣቸው የዞን መምሪያዎች አንዱ የደቡብ ወሎ ዞን ውሃና ኢነርጅ መምሪያ ሲሆን
1. የሲቪል ስራዎች የግንባታ ግዥ በተመለከተ
- ሎት 1. ገርባ ከተማ የውሃ ፕሮጀክት፣
- ሎት 2. ደጋን ከተማ የውሃ ፕሮጀክት፣
- ሎት 3. ለመድና ከተማ የውሃ ፕሮጀክት፣
- ሎት 4. ቢስቲማ ከተማ የውሃ ፕሮጀክት
- ሎት 5. ደጎሎ ከተማ የውሃ ፕሮጀክት የሚውል ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin/ ያላቸው፣
3. የተሰጠውን ፈቃድ ለሌላ ሰው ወይም ድርጅት አሳልፈው ያልሰጡ፣
4. ለሲቪል ስራዎች ግዥ ከሎት አንድ እስከ ሎት 5 ድረስ ላሉት ግንባታ ፕሮጀክቶች በውሃ ነክ ፈቃድ /WWC/ ያወጡ፣
5. አማካይ ተርን ኦቨር እና ፋይናንሽያል ሪሶርስ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
6. ደረጃ 5 እና በላይ ያላቸው፣
7. በ2016 ዓ.ም የሙያ ፈቃድ እና የባለሙያዎቻቸውን የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያሳደሱ፣
8. ለግንባታው የሚያስፈልጉ ማሽነሪዎችን እንደ ሚክሰር ዌልድንግ ማሽንና መሰል ግብአቶችን ማቅረብ የሚችሉ፣
9. ለነባር ተቋራጮች የትልልቅ መጠጥ ውሃ የመልካም ስራ አፈጻጸም የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ፣
10. የግዥ መጠኑ 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
11. ተጫራቾች በጨረታ ለመሣተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እና 2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሠነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
12. ተጫራቾች በኦርጅናል ዕቃ መገንባትና እና ያሸነፉትን የግንባታ ማቴሪያል በባለሙያ ማስፈተሽ እና የጥራት ደረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
13. የሚገነባ ግንባታ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሠነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
14. ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ሲሞሉ ቫትን ጨምሮ መሙላት አለበት፡፡
15. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን የማይመለስ ብር 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ማግኘት ይቻላል፡፡
16. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ብር የግንባታውን ጠቅላላ ዋጋ 1.5% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /C.P.O/ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
17. ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ ሊያሲዙ በመምሪያው የገቢ ደረሰኝ ቆርጦ ኮፒውን ከኦርጅናል ሰነዱ ጋር መታሸግ አለባቸው፡፡
18. አሸናፊው አካል የአሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የሚያስይዝ ይሆናል፡፡
19. ውድድሩ የሚካሄደው በየሎቱ በጥቅል ድምር ነው፡፡
20. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋና እና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ በግዥ ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ ቀናት የጨረታ ሰነዱን መግዛትና በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
21. ጨረታው ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው/ በተገኙበት በግዥና ንብ/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 7 በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይታሸጋል፡፡ በዚሁ ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ የመክፈቻው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
22. በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 7 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 033 111 6134 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 033 111 8118/19 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
23. በመ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የደቡብ ወሎ ዞን ገንዘብ መምሪያ