![South Ethiopia Roads Authority](https://diretenders.com/wp-content/plugins/wp-job-manager/assets/images/company.png)
South Ethiopia Roads Authority
አዲስ ዘመን
(Jan 06, 2025)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ደኢመባ 04/2017
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች ባለሥልጣን ለሥራ ክፍሎች አገልግሎት የሚውል
- በሎት አንድ አላቂ የጽህፈት መሳሪያዎች
- በሎት ሁለት ቋሚ ዕቃዎች/ኤሌክትሮኒክስ ማለትም ላፕቶፕ እና ዴስክ ቶፕ ኮምፒውተሮች/፣
- በሎት ሦስት አላቂ የጽዳት ዕቃዎች እና
- በሎት አራት የደንብ ልብስ ግዥ ብቁ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቸቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችላቸውን የዘመኑ ግብር የተከፈለበትን ከሚፈለገው አገልግሎት የተዛመደ የንግድ ሥራ ወይም የአገልግሎት ሥራ ፈቃድ፣ ከሃምሳ ሺህ ብር በላይ ላላቸው ግዢዎች የቫት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው ማስረጃ፣ በአቅራቢነት የተመዘገቡ ለመሆናቸው የምዝገባ ማስረጃ እና በጨረታ ለመሳተፍ ከሚመለከተው የመንግስት አካል የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር ብቻ/ በመክፈል ከባለሥልጣኑ ዋና መ/ቤት የቢሮ ቁጥር 05 መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታው ዋጋ ጨረታው ከተከፈተበት ጊዜ ጀምሮ ለሰላሳ /30/ ቀናት ፀንቶ መቆየት ይኖርበታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ የሚወሰነው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተመለከቱት መስፈርቶች መሰረት ነው፡፡
- አቅራቢዎች ጨረታውን አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ኮፒ ለዚህ ተግባር በተዘጋጀ ሳጥን ገቢ የሚያደርጉት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ድረስ ይሆናል፡፡ ጨረታው በዚያኑ ቀን ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ለሎት አንድ ብር 15,000.00 /አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ ፣ ለሎት ሁለት ብር 15000.00/ አስራ አምስት ሺህ ብር የ ለሎት ሦስት ብር 5000.00 /አምስት ሺህ ብር ብቻ እና ለሎት አራት ብር 5,000.00/አምስት ሺህ ብር ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ቼከ ወይም በባንክ ዋስትና ወይም በግዥ መመሪያው መሠረት አቅራቢው በፈለገው በአንዱ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ዋስትና መልክ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- ተጫራቾች በጨረታው ደንብና መመሪያ መሠረት ጨረታቸውን ማቅረብ አለባቸው፡፡ ከጨረታው ደንብና መመሪያ ውጭ የሚቀርብ ማንኛውም ጨረታ ተቀባይነት የለውም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ ተጫራቾች የሚከተለውን አድራሻ መጠቀም ይችላሉ፡፡
በደቡብ መንገዶች ባለሥልጣን የግብዓት አቅርቦት ባለሥልጣን አስደሥራ ሂደት የፖስታ ሳጥን ቁጥር 404
ስልክ ቁጥር፡- 046-13-15-012/09 16 866 262/09 23 690 085
የደቡብ ኢትዮጵያ መንገዶች
ባለሥልጣን