
South Achefer Woreda Court
በኩር
(Jan 06, 2025)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በባ/ዳርና አካ/ከፍ/ፍ/ቤት የደቡብ አቸፈር ወረዳ ፍ/ቤት ለመ/ቤታችን የሚያስፈልጉ አመታዊ ግዥ ማለትም
- ሎት 1. የጽ/መሳሪያ፣
- ሎት 2. ህትመት ፣
- ሎት 3. የጽዳት ዕቃዎች፣
- ሎት 4. የእጅ መሳሪያ ፣
- ሎት 5. ቋሚ ዕቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድር መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳዳር ትችላላችሁ፡፡
- በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸዉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን/ ያላቸዉ፡፡
- የግዥዉ መጠን 200,000.00 /ሁለት መቶ ሽህ /ብርእና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸዉን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸዉን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸዉ ጋር አያይዘዉ ማቅረብ አለባቸዉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ዘወትር በስራ ሠዓት በእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 20.00/ሃያ ብር/ በመክፈል ደ/አቸ/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ቢ/ቁ 11 መግዛት ይቻላል፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ(ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት የዕቃዉን ጠቅላላ ዋጋ አንድ በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸዉ፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁስት ቅጂዎች ማለትም ዋና እና ቅጂ በማለት በየምድቡ በተለያየ ፖስታ በማድረግ በጥንቃቄ በማሸግ በደ/አቸ/ወ/ፍ/ቤት ግ/ፋ/ን/አስ/ደ/ የስራ ሂደት ክፍለል ቢሮ ቁጥር 11 በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይቻላል፡፡
- ጨረታው በአየር ላይ የሚቆየው ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ብቻ ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን በ16ኛዉ ቀን በስራ ስዓት ከጠዋቱ በ2:30 ታሽጎ በ3፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በግልጽ የሚከፈት ሲሆን የሚከፈትበት ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥስው የስራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 የቅሬታ ቀናት በኋላ በ5 ተከታታይ ቀናት 10% የዉል ማስከበሪያ በማስያዝ ዉል መዉሰድ አለበት፡፡ እንደዉሉ ባይፈፀም ግን የጨረታ ማስከበሪያዉ ለመንግስት ገቢ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ውድድር የሚካሄደው በየሎቱ ጥቅል ድምር ስለሆነ ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ሎት ሁሉንም መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ በጥቅል ድምር አሸናፊ ለሚለይባቸው እቃዎች ስአንድም እቃ ዋጋ አለመሙላት ከጨረታ ውድድር ውጭ ያደርጋል፡፡
- መ/ቤቱ በጨረታ ከሚገዛው ዕቃ መጠን እስከ 20 በመቶ መጨመር ወይም መቀነስ ይችላል፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች ማስጫኛና ማውረጃ እንዲሁም ትራንስፖርት ወጭውን ችሎ ደ/አቸ/ወ/ፍ/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- መ//ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፤የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ መሆን የለበትም ስርዝ ድልዝ ከሆነ ፓራፍ መደረግ ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊ የሆነው ድርጅት ለሰነድ ምርምራ አገልግሎት ክፍያ ራሱ የሚከፍል ይሆናል፡፡
- በጨረታ ማስታወቂያው ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያ ቁጥር 1/2003 መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 223 01 60 በመደወል ቢሮ ቁጥር 11 በአካል በመምጣት መጠቅ ይችላሉ፡፡
ደቡብ አቸፈር ወረዳ ፍርድ ቤት