Dessie Surrounding Woreda F/E/D/B
አዲስ ዘመን
(Jan 07, 2025)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የደሴ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል
- ሎት 1 የስፖርት ትጥቅ
- ሎት 2 ሞንታርቦ
- ሎት 3 የመኪና ጎማ ከነካለማደሪያው
ከተራ ቁጥር 1-3 የተዘረዘሩትን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት
- በዘርፉ ህጋዊ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል
- በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ያላቸው
- የግዥ መጠኑ 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና ከዚያ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /AT/ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይ መሆን አለባቸው፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ
- ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 6 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የጨረታውን ሰነድ ከደሴ ዙ/ወ/ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) ለእያንዳንዱ ሰነድ በመክፈል መግዛት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ከ29/4/2017 ዓ.ም እስከ 13 /5/2017 ዓ.ም በአየር ላይ ይውላል፡፡
- ጨረታው በ14/5/2017 ዓ.ም 3፡30 ታሽጎ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ኦሪጅናል ዕቃ መሙላትና ያሸነፉበትን ዕቃ በባለሙያ ማስፈተሽ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ ዕቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን⁄ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በሰነዱ ላይ ሲሞሉ ከእያንዳንዱ የዕቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ መሙላት አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሚያቀርቡት ዕቃ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፤ ተጫራቾች በጥሬ ገንዘብ ሲያስይዙ በጽ/ቤቱ የገቢ ደረሰኝ ቆርጠው ኮፒው ከኦሪጅናል ሰነዱ ጋር መታሸግ አለበት፡፡
- ተሸናፊ ተጫራቾች በመመሪያው መሰረት ያስያዙት 2% ሲፒኦ ከአምስት ቀን በኋላ ይመለስላቸዋል።
- አሸናፊው አካል ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ የሚያስይዝ ይሆናል፡፡
- የስፖርት ትጥቅን በተመለከተ በቀረበው ናሙና መሰረት ማቅረብ የሚችሉና ናሙናውን በስራ ሰዓት ግዥ ቢሮ በመገኘት ማየት ይችላሉ፡፡
- አሸናፊ ተጫራች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ወጪ በየሴክተሩ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- በጨረታው ላይ የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ ሁለት ቅጂዎች ማለትም ዋና ቅጂ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በማሸግ እስከ 14/5/2017 ዓ.ም ደሴ/ዙ/ወ/ግዥ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ እስከ 3፡30 ሰዓት ድረስ እንዲያስገቡ እየገለፅን ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ እለት ከቀኑ 4፡00 ሰዓት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ደሴ/ዙ/ወ/ግዥ ቢሮ ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 033-111-7763 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ማሳሰቢያ፡– አሸናፊው ድርጅት /ተጫራች ኦሪጅናል ዕቃ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
በአብክመ ገ/ቢሮ በደ/ወሎ መስ/ዞን የደሴ ዙሪያ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት