የኢትዮጵያ ኦፕቶሜትሪ ባለሙያዎች ማህበር
አዲስ ዘመን
(Jan 07, 2025)
ለሶስተኛ ጊዜ የወጣ አስቸኳይ ግልፅ ጨረታ
የኢትዮጵያ ኦፕቶሜትሪ ባለሙያዎች ማኅበር በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አዋጅ 113/211 በኤጀንሲው ቁጥር 2913 የተመዘገበ የሙያ ማኅበር ሲሆን ከህዳር 01/2016 እስከ ጥቅምት 30/2017 ያለውን የማኅበሩን የሂሳብ ሥራ በውጪ ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- የሰርቲፋይድ ቻርተርድ አካውንታንት የሆኑና ኦዲት የማድረግ ሕጋዊ የሙያ ፈቃድ እንዳላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በዘርፉ ለ2017 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ ወይም ጨረታው እስከሚከፈትበት ቀን ድረስ ሊያገለግል የሚችል የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ ክሊራንስ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት (የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት) እና 5000.00 ብር (አምስት ሺህ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያቀርቡ ሆኖ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣ ከ5 የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት አምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ቫትን ያካተተ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ፕሮፖዛል በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ ለማኅበራችን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድና መመሪያ እንዲሁም የጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከ2፡30-10፡00 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) በመክፈል አራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል ጀርባ ተስኒም ሕንጻ ሁለተኛ ፎቅ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኦፕቶሜትሪ ባለሙያዎች ማኅበር ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ሥራውን ሰርተው የሚጨርሱበትን ቀን በመጥቀስ ማስገባት የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- ተቋሙ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ተጨማሪ ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 09 84-753 931 በመደወል መጠየቅ ይቻላል፡፡
አድራሻችን፡– አራት ኪሎ፣ ቱሪስት ሆቴል ጀርባ፣ ተስኒም ሕንጻ አንደኛ ፎቅ፣
የኢትዮጵያ ኦፕቶሜትሪ ባለሙያዎች ማኅበር