Ethiopian Airlines Group (ETG)
አዲስ ዘመን
(Jan 08, 2025)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: -SSNT-T507
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የአውሮፕላን ሞተር ጥገና መሰረተ ልማት ማስፋፊያ ፕሮጀክት ( Engine Shop Facility Expansion Project) ዲዛይን፣ የኮንትራት አስተዳደር እና የግንባታ ቁጥጥር አገልግሎት የሚሰጡ ደረጃ የህንጻ ስራ ንግድ ፈቃድ ያላቸው የሀገር ውስጥ አማካሪ ድርጅቶችን እና የሲቪል ምህንድስና ፈቃድ ያላቸው አለም አቀፍ አማካሪ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ብቁ የሆኑ አማካሪዎች ጨረታውን እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
የሀገር ውስጥ ተጫራቾች የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT)
ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ጨረታዎች ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ አለም አቀፍ ተጫራቾች ደግሞ የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
የፕሮጀክቱ ማጠናቀቂያ ጊዜ በ300 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ይሆናል።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥር 16, 2017 ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (100.00 ብር) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E 99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T507 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ክፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ።
በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ሁለት ሺህ አምስት መቶ የአሜሪካን ዶላር (2,500.00 የአሜሪካ ዶላር) ወይም ተመጣጣኝ የኢትዮጵያ ብር የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.አ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና በኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስም ማስያዝ አለበት። ማንኛውም ኢንሹራንስ እና ቅድመ ሁኔታ ያለው የባንክ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ ጨረታው ከተዘጋበት ቀን ጀምሮ ለ20 ቀናት የሚቆይ ይሆናል። አየር መንገዱ ጨረታው የሚቆይበትን ጊዜ እንዲራዘምለት ተጫራቾችን የመጠየቅ መብት አለው።
ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በኤንቨሎፕ አሽገው ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ጥር 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 08፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መስሪያ ቤት የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን 9፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ:- የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ –ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ስትራቴጂከ ሶርሲንግ ክፍል
ስልክ ቁጥር 011-517-8918
ኢ–ሜይል: EskedarG@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።