Ethiopian Petroleum Supply Enterprise
አዲስ ዘመን
(Jan 07, 2025)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 22/2017
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ለ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የህትመት ውጤቶች ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
- አጀንዳ የ2018 (2025/2026)
- ካሌንደር የ2018 (2025/2026)
- የመልካም ምኞት መግለጫ ካርድ (Greeting Card)
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይነት ሰርተፊኬት (TIN No.) ያላቸው፡፡
- የገንዘብ ሚኒስቴር ባወጣው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀትና ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከሀገር ውስጥ ገቢ መ/ቤት የሚሰጣቸውን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ግብር ከፋይነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር ) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከድርጅቱ ግዥና ትራንስፖርት ክፍል ቢሮ ቁጥር 011 መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ( Bid Bond ) ብር 20,000.00 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 27/5/2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 602 ለዚህ በተዘጋጀው ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ27/5/2017 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ዕለት 4፡05 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 602 ይከፈታል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- ሜክሲኮ አደባባይ ወደሳርቤት በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ
ስስክ ቁጥር 011-551-32 88
ፖ.ሣ.ቁ 3375 አአ
የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት