Development Bank of Ethiopia Dessie District
አዲስ ዘመን
(Jan 06, 2025)
የድርድር የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደሴ ዲስትሪክት ከቀድሞው የሰሜን ምዕራብ ሪጅን ባህር ዳር የተረከባቸው ሰባት /07/ ደንበኞች የእህል ወፍጮ እንዲሁም አንድ /01/ ደንበኛ የዳቦ መጋገሪያ ፕሮጀክት እንዲያቋቁሙ ብድር ተፈቅዶላቸው አስፈላጊ የሆኑ ማሸነሪዎች ተገዝተውላቸው ወደ ስራ የገቡ ቢሆንም የሚጠበቅባቸውን ክፍያ በተዋዋሉት የብድር እና መያዣ ውል ስምምነት መሠረት ብድሩን ባለመክፈላቸው ንብረቶችን ባንኩ በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሠረት ተረክቦ በሐራጅ ጨረታ ገዥ ባለመቅረቡ በግምቱ ልክ ባንኩ የተረከባቸውን ንብረቶች ባሉበት ይዞታ ሁኔታ በድርድር ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ተ.ቁ |
የባለዕዳው የመያዣ ሰጭው ስም/ |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
የንብረቱ አይነት |
የንብረቱ አድራሻ |
የጨረታ ደረጃ
|
የድርድር ጨረታው የሚካሄድበት ቀን እና ሰዓት |
1 |
ነጋ ከበደ |
29,240 |
የእህል ወፍጮ |
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ በደቡብ ወሎ ዞን፣ ደሴ ከተማ አስተዳደር፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ፣ ደሴ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ውስጥ |
የድርድር
|
ማክሰኞ ጥር 27 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት
|
2 |
ኢብራሂም ሰይድ |
25,280 |
የእህል ወፍጮ |
|||
3 |
ሽፋው አየለ |
24.320 |
የእህል ወፍጮ |
|||
4 |
መሐመድ ጀማል |
42,000 |
የእህል ወፍጮ |
|||
5 |
ጌታቸው ሽፈራው |
25,600 |
የእህል ወፍጮ |
|||
6 |
ዘዉዱ ጌታሁን |
36,100 |
የእህል ወፍጮ |
|||
7 |
አለሙ ቸረኝ |
105.736 |
የእህል ወፍጮ |
|||
8 |
ታፈረ ገ/ህይወት |
2,600 |
የዳቦ መጋገሪያ |
ማሳሰቢያ፡–
- ተጫራቾች የድርድር ጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ ከፍያ ማዘዣ (CPO) ብቻ በማስያዝ የድርድር ጨረታ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን የድርድር ጨረታ ሰነዱን በደሌ ቅርንጫፍ ቀርበው አንድ መቶ ብር (100) ከፍያ በመፈፀም መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች በንብረቶች ላይ በጥቅል በተናጠል መጫረት ይቻላል።
- አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 (በአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።
- የድርድር ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደሴ ዲስትሪከት ቅጥር ግቢ ሲሆን ንብረቱን በአካል ማየት የሚፈልግ ተጫራች በዲስትሪክቱ ቢሮ በመምጣት ማየት ይችላሉ።
- አሸናፊው ድርጅት ግለሰብ ባሸነፈበት ዋጋ ላይ የሚታሰብ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰነ ግብሮችን፣ የስም ማዞሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዥው የጨረታ አሸናፊው ይከፍላል።
- ተጫራቾች በመንግስት የተቀመጠውን ቀረጥና ታከለ ከፍያ መፈፀም ይኖርበታል።
- በድርድር ጨረታ ላይ መገኘት የሚችሉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው፣ የታደሰ መታወቂያ እና (አንድ አራተኛ) በባንክ ከፍያ ማዘዣ (CPO) መያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- የድርድር ጨረታ ሳጥኑ ግልፅ ሆኖ ውስጡ ባዶ መሆኑን የድርድር ተጫራቾች ከተመለከቱት በኋላ በሰም በታሸገ ፖስታ የተዘጋጀውን ሰነድ የድርድር ጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደሴ ዲስትሪክት አንደኛ ፎቅ በሚገኘው ሎን ወርክ አውት ቡድን ቢሮ ማግኘት ይቻላሉ ወይም በስልክ 033 312-48-07/033-32-00-87 ደውሎ ማብራሪያ ማግኘት ይችላል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደሴ ዲስትሪክት