Addis Ababa Police
አዲስ ዘመን
(Jan 08, 2025)
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር AAPC NCB 005/2017 ዓ.ም
የአ/አበባ ፖሊስ በ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ ተሽከርካሪዎች እና የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ሲሆን፡-
ሎት |
የጨረታ ዓይነት |
የናሙና መለያ |
የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ መጠን |
|
001 |
የኤሌክትሪክ መኪና ሲቲ ባስ |
በኮሚሸኑ ስፔስፊኬሽን መሰረት |
500,000 |
00 |
|
ዚላ የአድማ ብተና ውሃ መርጫ ተሽከርካሪ |
በኮሚሸኑ ስፔስፊኬሽን መሰረት |
500,000 |
00 |
ለአጀብ ሰራ የሚውል 1250CC ሞተር ሳይክል ግዥ |
በኮሚሸኑ ስፔስፊኬሽን መሰረት |
500,000 |
00 |
|
የኤሌክትሪክ አውቶሞቢል ሳይረን ዊዝ ሂድ ያለው ተሽከርካሪ |
በኮሚሸኑ ስፔስፊኬሽን መሰረት |
500,000 |
00 |
|
002 |
በተሽከርካሪ ላይ የሚገጠም ሳይረን በድጋሚ የወጣ |
በኮሚሸኑ ስፔስፊኬሽን መሰረት |
50,000 |
00 |
003 |
የተለያዩ መድሃኒቶች እና የህክምና መሳሪያዎች |
በኮሚሸኑ ስፔስፊኬሽን መሰረት |
120,000 |
00 |
004 |
የላቦራቶሪ ፋይል ካብኔት |
በኮሚሸኑ ስፔስፊኬሽን መሰረት |
50,000 |
00 |
005 |
ለስፖርተኞች የውድድር ብስክሌት ግዥ በድጋሚ የወጣ |
በኮሚሸኑ ስፔስፊኬሽን መሰረት |
40,000
|
00 |
006 |
የህግ ተጠርጣሪ ቀለብ በድጋሚ የወጣ |
በኮሚሸኑ ፍላጎት መሰረተ |
30,000 |
00 |
007 |
የጀነሬተር ጥገና በድጋሚ የወጣ |
በኮሚሸኑ ስፔስፊኬሽን መሰረት |
20,000 |
00 |
008 |
የሊፍት ጥገና በድጋሚ የወጣ |
በኮሚሸኑ ስፔስፊኬሽን መሰረት |
20,000 |
00 |
009 |
የድረሱልኝ ጥሪ ማዕከል የአየር ማቀዝቀዣ |
በኮሚሸኑ ስፔስፊኬሽን መሰረት |
150,000 |
00 |
0010 |
የተለያዩ የፅህፈት መሳሪዎች |
ናሙና የሚቀርብበት |
20,000 |
00 |
0011 |
የተለያዩ የፅዳት ዕቃዎች |
ናሙና የሚቀርብበት |
20,000 |
00 |
0012 |
የተለያዩ ሲቪል ሰራተኞች አልባሳት |
ናሙና የሚቀርብበት |
20,000 |
00 |
0013 |
Supply design installation commissioning and testing media storage server and management software solution ግዥ በድጋሚ የወጣ |
በኮሚሸኑ ስፔስፊኬሽን መሰረት |
300,000 |
00 |
ስለዚህ፡- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን እና በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው ይመልከቱ የሚል ፅሁፍ በግልፅ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- የታደሰ የዘመኑን ንግድ ፍቃድ እና የታደሠ ንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው።
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ክሊራንስ ማቅረብ አለበት።
- አማራጭ ዋጋ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም።
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ተብሎ በተዘጋጀው ከባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.አ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችንና የዋጋ ማቅረቢያዎችን ፋይናንሻል ሰነዶች በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ መቅረብ አለባቸው።
- ማንኛውንም ተጫራቾች የሚያስገባው ሰነድ ፋይናንሻል እና ቴክኒካል የጨረታ ሰነድ አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የጨረታ ሰነዱን ቁጥር የሚጭረትበትን ዕቃ አይነት በትከክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታው ላይ ማህተም በመምታት ማስገባት ያለበት ሲሆን ፤ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያሲዙት ሲ.ፒ.ኦ. ከቴክኒክ ሰነዶች ጋር በአንድ ላይ ታሽገው መቅረብ አለባቸው።
- በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን ወይም አገልግሎቱን በራሳቸው ትራንስፖርት አበባ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የኮሚሽኑ ዋና መስሪያ ቤት ግምጃ ቤት ወይም በክፍል 6 በፍላጎት መግለጫው በተጠቀሰው የማስረከቢያ ቦታ ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው።
- በጨረታ ሰነድ በክፍል 6 ውስጥ በሚገኘው የፍላጎት መግለጫ ላይ በሚገለፀው መሰረት ጨረታ ሰነዱ ላይ በቀረበው መሠረት ናሙና ማቅረብ አለበት
- ተጫራቾች ያቀረቡት ናሙናም ሆነ አሸናፊ መሆናቸው ሲረጋገጥ ያቀረቧቸው ዕቃዎች ኮሚሽኑ ባወጣው ፍላጎት መግለጫ/ sepecification/መሰረት መሆኑን በኮሚሽኑ የጥራት ኮሚቴ ወይም በኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ኤጀንሲ አማካኝነት የሚረጋገጥ ይሆናል
- ተጫራቾች አራዳ ጊዮርጊስ ቤ/ክርስቲያን ከፍ ብሎ በሚገኘው የኮሚሽኑ ዋና መስሪያ ቤት 5ኛ ፎቅ ግዢ ጽ/ቤት ቢሮ ቀርበው በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ፣
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ እንዲሁም በማግስቱ በ11ኛው ቀን እስከ ጠዋት 4፡30 ሠዓት ድረስ ጨረታው ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ በኮሚሽኑ ግዢና ፋይናንስ 5ኛ ፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
- በጨረታ ሰነዱ ክፍል 2 ላይ በሚጠቀሰው ቀን ከጠዋት 4፡30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 5፡00 ሰዓት ሲሆን በመ/ቤቱ 5ኛፎቅ ትንሹ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 512 ይከፈታል፣
- የጨረታው መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ ቀጥሎ ባለው መደበኛ የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው 4፡30 ሰዓት ታሽጎ 5፡00 ሲሆን ይከፈታል።
- ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ የረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስ.ቁጥር፡- 011 862-58-00 (011 111 0448)
የአ/አበባ ፖሊስ