Adama Hospital Medical College
አዲስ ዘመን
(Jan 08, 2025)
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የአዳማ ሆስፒታል ሚዲካል ኮሌጅ በ2017 የበጀት ዓመት፡–
- 1. የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች
- 2. የተለያዩ የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦች እና
- 3. እንጃራ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት መስፈርቶች የምታሟሉ ነጋዴዎች መወዳደር ትችላላችሁ፡፡
- የ2017 ዓ.ም የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ በዘርፉ ያላችሁ::
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ ስለመሆን መረጃ ማቅረብ የሚችል
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ፅ/ቤት በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ መመዝገባችሁን የሚያረጋግጥ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ ግዥ መ/ቤት ድረስ በራሱ ወጪ ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጨረታ ሰነድ ኮፒና ኦርጅናል ለየብቻ በተለያየ ፖስታ ማሸግ አለባቸው፡፡
- ስርዝ ድልዝ ያለው፤ የማይታይ የጨረታ ሰነድ ወይም የዋጋ ዝርዝር ተቀባይነት የለውም፡፡
- ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ዋጋ 10% ማስያዝ የሚችል፡፡
- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከኮሌጁ ግዥና ፋይናንስ የስራ ሂደት ከፍል ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ በእያንዳንዱ ብር 100 /አንድ መቶ ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ አለባቸው።
- የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች ጨረታው የሚከፈተው በ16/05/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የተለያዩ የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦች ጨረታው የሚከፈተው በ20/05/2017 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- እንጀራ ጨረታው የሚከፈተው በ20/05/2017 ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚሞሉትን ዋጋ በመስሪያ ቤቱ ሰነድ ብቻ ላይ መሆን አለበት፣
- የጨረታው ማስከበሪያ ለተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች ፤ ለተለያዩ የምግብ ሸቀጣ ሸቀጦች እና ለእንጀራ ለእያንዳንዱ ለየብቻ 10,000 (አስር ሺህ) “CBE፣ CBO እና Sinqe” በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 022 812 3956 ደውለው መረዳት ይችላሉ፡፡
የአዳማ ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ