ANRS Building Construction Works Construction Enterprise
አዲስ ዘመን
(Jan 08, 2025)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 10/2017
የአማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት እየገነባው ላለው ለጎንደር ጉምሩክ ግንባታ አገልግሎት የሚውል ፒቪሲ ጅፕሰም ሲሊንግ ታይል እና አርምስትሮንግ አቅርቦትና ገጠማ ሥራ ህጋዊና ብቃት ያላቸውን አቅራቢዎች እና ፋብሪካዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤
- በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የንግድ ፈቃድ ለማደስ ግብር ስለመክፈላቸው የሚሰጥ ማስረጃ ያለው/ያላት፤ ጨረታ ለመካፈል የሚያስችል ሰርተፍኬት
- ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ቫትን ጨምሮ የጠቅላላ ዋጋውን 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም (unconditional bank guarantee/ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ባ/ዳር ከተማ አማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ቀበሌ 11 እና አ/አበባ ለገሀር አመልድ ህንፃ 7ኛ ፎቅ በሚገኘው ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 02 የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ/ በመክፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀናት ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኦርጅናልና ኮፒውን በመለየት በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ባ/ዳር ዋናው መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በዕለቱ 8፡00 ሰዓት ሳጥኑ ታሽጎ 8፡30 ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን እስከ ቀኑ 8፡00 ሠዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው የሚከፈተው ባህር ዳር ዋናው ቢሮ አንደኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 108 የግን/ግብ/ግዥ እና አቅርቦት ኬዝ ቲም ቢሮ ክፍል ነው፡፡
- ውድድሩ በሎት /በጥቅል ዋጋ የሚታይ ሲሆን በሚቀርበው ዋጋ በማወዳደር አሸናፊው ሊለይ ይችላል፡፡
- ዝርዝር የጨረታ መመሪያው እና የውል ይዘቱ በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተገለፀ ስለሆነ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በማንበብ ዋጋቸውን በጨረታ መመሪያው መሰረት መሙላት አለባቸው፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር፡–
ባህርዳር 058 218 0538/ 09-13-10-96-11/09-13-27-60-57
አዲስ አበባ ፡– 011-126-5652/-126-5145/09 18 705 036
የአማራ ህንፃ ሥራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት