Robe Teachers College
አዲስ ዘመን
(Jan 06, 2025)
የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር KBR. 4/2017
የሮቤ መምህራን ኮሌጅ ለ2017 በጀት ዓመት ወደ ኮሌጃችን ተመድበው ለሚገቡ ተማሪዎች ለምገባ አገልግሎት የሚውል የበሰሉ ምግቦች እና ትኩስ መጠጦችን፣ በኮሌጁ ቅጥር ግቢ ውስጥ አብስሎ (አዘጋጅቶ) ከሚያቀርብ አካል አወዳድሮ ገዝቶ ለተማሪዎች ማቅረብ ይፈልጋል።
ስለዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ የንግድ ድርጅቶች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።
- ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል የሚያስችል በሚወዳደሩበት የንግድ ዘርፍ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር ከፍለው ለ2016/2017 ዓ.ም የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ (Trade License) ወይም የዘመኑን ግብር ስለመክፈሉ የሚገልጽ ከገቢዎች ባለሥልጣን ቢሮ የተጻፈ ደብዳቤ፣ የንግድ ምዝገባ ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት (Value Added Tax /VAT)፣ የግብር ከፋይ መለያ ሰርተፍኬት (Taxpayer Registration Certificate/TIN) ፣ የአቅራቢነት ምዝገባ ማስረጃ (Supplier List Certificate) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት የሥራ ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በሲንቄ ባንክ የሂሳብ ቁጥር 1072925211214 በመክፈል የከፈሉበትን የባንክ ደረሰኝ (Bank Deposit Slip) በመያዝ ከሮቤ መምህራን ኮሌጅ እቅድ፣ ግዥ፣ ፋይናንስ እና ንብረትአስተዳደር ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) የያዘ በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) በሮቤ መምህራን ኮሌጅ ስም በማስያዝ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት የሥራ ቀን ጀምሮ የሚጫረቱባቸውን ሰነዶች በመግዛት ዋናውን (Original) ፋይናንሻል (ዋጋ የተሞላባት) ሰነድ፤ ፋይናንሽያል ቅጅ (ዋጋ የተሞላበት ኮፒ ሰነድ) እንዲሁም ቴክኒካል ኦሪጂናል ሰነድ በተለያዩ ፖስታዎች አሽገው ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታው ሳጥን እስከሚታሸግበት ዕለት እና ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ በሮቤ መምህራን ኮሌጅ ስም ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ (ሲፒኦ) ከቴክኒካል ኦሪጂናል ሰነድ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለጨረታ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ዋጋው ሲፃፍ ስርዝ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መጻፍ አለበት።
- በእያንዳንዱ ሰነድ እና የታሸገ ፖስታ ላይ የድርጅቱ ኃላፊ ፊርማ እና ማህተም መኖር አለበት።
- ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል።
- ተጫራቾች ማሸነፋቸው በደብዳቤ ከተገለፀላቸው ከ5ኛው ቀን በኋላ ከ6ኛው ቀን ጀምሮ በ15 የሥራ ቀናት ውስጥ ሮቤ መምህራን ኮሌጅ ቀርበው ውል መፈራረም አለባቸው።
- አሸናፊው የሚያቀርበው ምግቦች እና ትኩስ መጠጦችን በኮሌጁ ቅጥር ግቢ ውስጥ አብስሎ (አዘጋጅቶ) መመገብ አለበት።
- ተጫራቾች ሙሉውን መረጃ ለጨረታ ከተዘጋጀው ሰነድ ላይ ማግኘት ይችላሉ።
- ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 13 223 605/09 30 292 416 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
ሮቤ መምህራን ኮሌጅ