
Wolaita Zone Sodo Surrounding Woreda FEDB
አዲስ ዘመን
(Jan 23, 2025)
ለበርካታ ዓመታት (ዕድሜ ጠገብ ) እንጨቶች
ሽያጭ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
ወላይታ ዞን የሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በኮካቴ ማራጫሬ ችግኝ ጣቢያ ውስጥ ለበረካታ ዓመታት (ዕድሜ ገብ) እንጨቶች ማለትም ፓይነስ ፓቹላ፤ ባህርዛፍ የፈረንጅ ጽድ እና ግራቭሊያ እንጨቶችን ለተለያዩ ዓለማ ላይ የሚውል ደን ዛፎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፡-
- ማንነቱን የሚገልጽ የታደሰ መታወቂያ ፎቶ ኮፒ እና የጨረታ ሰነድ የገዙበት ደረሰኝ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ከላይ የተገለጹ ፓይነስ ፓቹላ ፤ባህርዛፍ የፈረንጅ ጽድ እና ግራቭሊያ በዝርዝር የያዘውን የመወዳደሪያ ሰነድ ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለጨረታ ከሚያስገበው ገንዘብ መጠን ጠቅላላ 4% (አራት በመቶ) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ በጽ/ቤቱ ደረሰኝ ገቢ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሣጥን ጋዜጣው ከወጣበት 15 ተከታታይ ሥራ ቀናት ቀጥሎ በሚውለው የሥራ ቀን ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ታሽጐ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ከሰዓት 8፡45 ሰዓትበቢሮ ቁጥር 4 ይከፈታል፡፡
- የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ እንደተረጋገጠ ያሸነፈበትን ዋጋ በሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የባንክ አካውንት ሙሉ በሙሉ ገቢ ሲያደርግ ያሸነፈውን ደን እንጨቶችን ወዲያውኑ ይረከባል፡፡ ሌሎች ዝርዝር ሂደቶች በጨረታ ሰነድ የሚካተቱ ይሆናል፡፡
- አሸናፊ በሆኑበት ደን እንጨቶች ሽያጭ በተሰጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ ስምምነት ውል ለመግባት ፍቃደኛ ካልሆኑ የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግሥት ገቢ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ገዝተው የገዙበትን ደረሰኝ በመያዝ ሶዶ ዙ/ወ/አከባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ጋር በመሆን በኮካቴ ማራጫሬ ችግኝ ጣቢያ ውስጥ ያለውን የፓይነስ ፓቹላ ፤ባህርዛፍ የፈረንጅ ጽድ እና ግራቭሊያ እንጨቶችን ሄደው ማየት ይችላሉ፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 046-180-6026 ደውለው
ማነጋገር ይችላሉ፡፡
ወላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ፋይ/ጽ/ቤት