Gamo Zone Gacho Baba Woreda Finance Office
አዲስ ዘመን
(Jan 07, 2025)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ ምንግስት የጋሞ ዞን የጋጮ ባባ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለወረዳው ሴክተር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል ፈርኒቸር ዕቃዎች ግዥ በውል የሚታሰር ግዥ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ መሠረት አወዳደሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት:
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው።
- የዘመኑን የስራ ግብር የከፈላችሁና ሰርተፍኬት ያላቸው።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ተመዝጋቢ
- አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
- ያሸነፈበትን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ወጪ እስከ ጋጮ ባባ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ማቅረብ የሚችል።
- የጥራት ችግር ያለባቸውን ዕቃዎችን መመለስና መቀየር የሚችል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ተትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከጋጮ ባባ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥ ክፍል በመቅረብ 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።
- ጨረታው የሚከፈተው 16ኛ የስራ ቀን ከሆነ ብቻ ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት ታሽጎ 5፡30 ሰዓት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መክፈቻ ሂደት አያስተጓጉልም።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ብቻ በጥሬ ገንዘብ ፣በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ ቢድ ቦንድ እና CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ሞልተው ያቀረቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን መግለጽ አለባቸው፡ ካልተጠቀሰ ግን ቫትን ያካተተ ተብሎ ይወሰዳል።
- የጨረታ አሸናፊ የሚለየው በዕቃው Item by item ዝቅትኛ ዋጋ ባቀረበ ይሆናል።
- ክፍያ የሚፈፀመው አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸውን ዕቃዎች በራሱ ትራንስፖርት እስከ ጋጮ ባባ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ድረስ ሲያቀርብ የጥራት ደረጃቸው ሲረጋገጥ ብቻ ክፍያ ይፈፀማል።
- ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 251-913 868 795/251-910 450 877 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጋሞ ዞን የጋጨ ባባ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት