
Kolefe Keranio Sub City Wereda 7 Administration Finance Office
አዲስ ዘመን
(Jan 23, 2025)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2017
በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ፋ/ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት 2ኛ ዙር ግልጽ ጨረታ
- ሎት 1 ደንብ ልብሶች
- ሎት 2 የጽዳት እቃዎች
- ሎት 3 አላቂ የቢሮ እቃዎች
- ሎት 4 ልዩ ልዩ እቃዎች
- ሎት 5 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና
- ሎት 6 የትራንስፖርት እና የጭነት አገልግሎት
- ሎት 7 የሕትመት ስራ
- ሎት 8 መስተንግዶ አገልግሎት
- ሎት 9 የዲኮር እና የድንኳን ኪራይ
- ሎት 10 የፈርኒቸር ጥገና
- ሎት 11 ቋሚ እቃዎች
- ሎት 12 የጉልበት ስራ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ተጫራቾች በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሰውን መስፈርት የሚያሟሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል፡፡
2. የሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች በመስኩ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና በአቅራቢነት መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ቲን (TIN) ሰርተፍኬት ኮፒውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችል ይሆናል፡፡ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር ብቻ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ከፋይናንስ ጽ/ቤት መግዛት ይቻላል፡፡
3. ተጫራቾች በቅድሚያ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) የሚጫረቱበት
- ሎት/1 የደንብ ልብሶች ግዢ ብር 2500
- ሎት/2 የጽዳት እቃዎች 2200
- ሎት/3 አላቂ የቢሮ እቃዎች 2000
- ሎት/4 ልዩ ልዩ እቃዎች 1000
- ሎት/5 የኤሌክትሮኒክስ ጥገና 3000
- ሎት/6 የትራንስፖርት እና የጭነት አገልግሎት 4000
- ሎት 7 የህትመት ስራ 3000
- ሎት/8 የመስተንግዶ አገልግሎት 2300
- ሎት/9 የዲኮር እና የድንኳን ኪራይ 2000
- ሎት/10 የፈርኒቸር ጥገና 2300
- ሎት 11/ ቋሚ እቃዎች 1500 ስራ
- ሎት 12 /የጉልበት ስራ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4. የመጫረቻ ሰነዱ በታሸገ ኢንቨሎፕ ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት እና በማሸግ ከጨረታዉ መዝጊያ ቀንና ሰዓት በፊት የጨረታ ማስገቢያ ቦታ ኮ/ቀ/ክ/ ከ/ወ/07 ፋ/ጽ/ቤት 3ኛ ፎቅ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀዉ የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸዉ፡፡
5. ጨረታዉ በ11ኛዉ ቀን ላይ ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዚያዉ እለት ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በቢሮዉ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል ይህ ቀን የበዓል ቀን ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ይከፈታል።
6. አንድ ተጫራች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም እንዲሁም አማራጭ ይዞ መቅረብ አይቻልም፡፡
7. በግዥ አዋጁ መሰረት ለጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ልዩ አስተያየት የሚደረግ ሲሆን በጥቃቅንና አነስተኛ ስለመደራጀታቸዉ የሚገልፅ ከአደራጃቸዉ ተቋም በጽ/ቤቱ ኃላፊ የተረጋገጠ የዋስትና ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
8. የአንዱ ዋጋ የማይለወጥ በመሆኑ ተጫራቾች በትክክል መሙላት ይጠበቅባቸዋል እንዲሁም የዕቃዉ ጥራትና ዋጋ ከግምት በማስገባት እንዲሞሉ፡፡
9. የትራንስፖርት አገልግሎት አቅራቢዉ ወረዳዉ እስቶር (ዕቃ ግምጃ ቤት) ድረስ አምጥቶ የሚያስረክብ መሆኑን ከግንዛቤ ዉስጥ እንድታስገቡ፤
10. የዕቃዉን 20 ፐርሰንት መጨመር ወይም መቀነስ መ/ቤቱ የሚችል መሆኑን እና ጠቅላላ ዋጋዉን 25 ፐርሰንት 6 ወር ድረስ ጨምሮ ሊይዝ የሚችል መሆኑን፤
11. ተጫራቹ ለተወዳደሩባቸዉ ሎቶች ሳምፕል (ናሙና) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
12. ቢሮዉ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- የጉልበት ስራ ለሚወዳደሩት በስራ እድል ፈጠራ የተደራጁ ቢሆን ደብዳቤ እና የቲን ቁጥር ብቻ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
አድራሻ፡- ኮ/ቀ/ክ/ከ /ወ/ 07 ቤቴል እሳት አደጋ ፊት ለፊት በ40 ሜትሩ መንገድ በኩል ነዉ
ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር 011 369 6634 ይደውሉ፡፡
በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ ከተማ ወረዳ 07 አስተዳደር ፋ/ ጽ/ቤት