![North Shewa Zone Ataye City Administration Finance and Economic Cooperative Bureau](https://diretenders.com/wp-content/plugins/wp-job-manager/assets/images/company.png)
North Shewa Zone Ataye City Administration Finance and Economic Cooperative Bureau
አዲስ ዘመን
(Jan 07, 2025)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር 02/2017
በአብክመ ሰሜን ሸዋ ዞን የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በስሩ ለሚገኙ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች የመኪና ጎማ፣ የግንባታ ማቴሪያል፣ ፌሮ ብረት እና ሲሚንቶ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም ፡-
- በዘርፉ የወጣ ንግድ ፈቃድና በዘመኑ የታደሰ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የምትችሉ
- መለያ ቁጥር /ቲን/፣ የቫት ተመዝጋቢነት የተመዘገባችሁበትን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ የምትችሉ
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎችን በግልጽ የሚታይ ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው
- የሚገዙ ዕቃዎች አይነትና ዝርዝር መግለጫ ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ
- ተጫራቾች በቀረበው ዝርዝር መስረት የምታቀርቡበትን ከጥቅል ዋጋው ላይ 1% CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ በአጣ/ከ/አስ/ገንዘብ /ጽ/ቤት ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የምትችሉ
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 300 ብር /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከኣጣ/ከ/አስ ገንዘብ ጽ/ቤት መውሰድ ትችላላችሁ
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የካላንደር ቀናት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ከአጣ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ዘወትር በሥራ ሰዓት በመቅረብ መግዛትና ለዚሁ በተዘጋጀው በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ትችላላችሁ፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከሰዓት በኋላ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ጨረታው በ16ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል
- ተጫራቾች በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ ሞልተው ማቅረብ አይችሉም
- በጨረታ አሸናፊው ተጫራች ለጽ/ቤቱ ባቀረበው የዋጋ ዝርዝር ከጠቅላላ ዋጋ ከነቫቱ 10% የውል ማስከበሪያ በCPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ብቻ በማስያዝ ውል የመፈረም ግዴታ ያለበት መሆኑን ማወቅ አለበት፤
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ማሳሰቢያ ፡-
- መረጃ መጠየቅ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 033 661 0688 ላይ ደውለው መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ለምትጫረቱበት ሎት ተዛማጅ የሆነ ንግድ ፈቃድ ኮፒ ማቅረብ ይኖርባችኋል
- ጨረታውን የምናወዳድረው በሎት ስለሆነ በሎቱ ውስጥ ላሉ ዕቃዎች በሙሉ ዋጋ መሞላት አለበት ካልተሞላ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
በሰሜን ሸዋ ዞን የአጣዬ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ
ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት አጣዬ