Angolela and Tera Woreda F/E/D/Bureau
አዲስ ዘመን
(Jan 06, 2025)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 05/2017
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን የአንጐለላና ጠራ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ለወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት የሚውሉ የተለያዩ የላብራቶሪ የትምህርት እቃዎች እና የተለያዩ የትምህርት አጋዥ መጽሃፍቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የምትፈልጉ:
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር TIN NO/ ያላቸውና ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ/ ብር በላይ ዋጋ ባላቸው ግዥዎች የሚሳተፉ ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ እና ለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- እቃዎቹን በአንድ ጊዜ በአይነት፣ በመጠን፣ በጥራት ሳያጓድል ማቅረብ የሚችል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ባቀረቡት ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ፣ ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው ስማቸውን፣ አድራሻቸውን በመጻፍ እና በመፈረም የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋና እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን 2% በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከተፈቀደላቸው የታወቁ ባንኮች የሚሰጥ በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ክሬዲት ወይም ገ/ኢ/ት/ዋና ጽ/ቤት በመሂ ያስያዙበትን ደረሰኝ ከኦርጅናል ዋጋ ማቅረቢያ ውስጥ መያያዝ አለበት፡፡ የእቃ ግዥ መ/ቤቱን፣ የተጫራቹን ስምና አድራሻ፣ እንዲሁም የግዥውን የእቃ አይነት በመጥቀስ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከሰዓት 8:00 ሰዓት ድረስ በጽ/ቤቱ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በዚሁ እለት በ16ኛው ቀን ከሰአት 8:00 ሰዓት ይታሸግና በእለቱ ከሰዓት 8:30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም።
- 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ ጨረታው በሚቀጥለው በመንግስት የሥራ ቀን ይከፈታል፤
- መ/ቤቱ ጨረታውን በሎት ያወዳድራል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ማንኛውንም አይነት ግብር የሸፈነ መሆን አለበት፡፡
- አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት አን/ጠ/ወ/ንብረት ክፍል ድረስ በመውሰድ ማስረከብ ይጠበቅበታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በአን/ጠ/ወ/ገ/ጽ/ቤት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከሚከፈትበት ቀን ድረስ በመንግስት የስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ፤
- በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ላይ ያልተገለፀ በተጫራቾች መመሪያ እና በኦርጅናል ሰነዱ ላይ በዝርዝር ስለሚገለጽ ዝርዝራቸውን በትኩረት ማየት ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ጽ/ቤቱ የሚገኘው ከአ/አበባ በስተሰሜን 110 ኪ/ሜ ርቀት በደ/ብርሃን መስመር ላይ ነው፡፡
- ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011-6 32-01-47 ወይም 011-6 32-03-04 ደውለው ይጠይቁ።
በአብክመ ገንዘብ ቢሮ በሰሜን ሸዋ ዞን የአንጎስላና ጠራ
ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት