Yigem Health Care Center
አዲስ ዘመን
(Jan 06, 2025)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ የይገም ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ለአገልግሎት የሚውሉ፡-
- ሎት 1 የፅህፈት መሳሪያዎች፣
- ሎት 2 የደንብ ልብስ፣
- ሎት 3 የተለያዩ ህትመቶች፣
- ሎት 4 የፅዳት እቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሳተም ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት፡-
- በዘርፉ የተሰማሩና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር ያላቸው፡፡
- የግዥው መጠን ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1 እስከ 3 የተጠቀሱትና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የሚገዙ እቃዎችን እና የሚታተሙት ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታው ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ / CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ለእያንዳንዱ ሎት ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ፊርማቸውንና የድርጅታቸውን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
- በመጫረቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ፖስታዎች ማለትም አንድ ኦሪጅናል እና አንድ ኮፒ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በይገም ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን ጨረታው በተዘጋበት ቀን በ4፡30 ሰዓት ላይ በመንዝ ማማ ምድር ወረዳ በይገም ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 1 ውስጥ በይፋ ይከፈታል፡፡ ባይገኙም ከመከፈት አይታገድም፡፡
- ጨረታው የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር ብቻ/ በመክፈል ከመንዝ ማማ ምድር ወረዳ በይገም ጤና አጠባበቅ ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 1 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን ንብረት በራሳቸው ወጪ ወደ ጤና ተቋሙ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-09-11-09-41-51/ 0920-33-20-76 ደውስው ይጠይቁ፡፡
በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የመንዝ ማማ ምድር ወረዳ የይገም ጤና አጠባበቅ ጣቢያ