Misrak Goh General Secondary School
አዲስ ዘመን
(Jan 07, 2025)
ሁለተኛ ዙር የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ምስራቅ ጎህ አጠቃላይ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2017 ዓ.ም በጀት አመት ለቢሮና ለትምህርት አገልግሎት የሚውሉ፦
- ቋሚ ዕቃዎች፣
- የፅህፈት መሳሪያ፣
- የደንብ ልብስ፣
- የፅዳት ዕቃዎች፣
- አላቂ የህክምና ዕቃዎች፣
- የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣
- የቧምቧ ዕቃዎችና
- የኤክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታ በማሟላት መጫረት ይችላሉ።
- የታደሰ የንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለዚህም መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
- በመንግስት ንብረት ግዥ አስተዳደር ኤጄንሲ በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
- የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- የግብር ከፋይ መለያ (Tin) ቁጥር ሊኖራቸው ይገባል።
- የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ 2% በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ጥራትና ደረጃውን የጠበቀና ለዚህም ለእያንዳንዱ ዕቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በት/ቤቱ በግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን(ግዥ ክፍል) ቢሮ ቁጥር 4 መውሰድ ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙበት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ በግልፅ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በተጠቀሰው የስራ ቀናት ዘወትር የስራ ሰአት በ/ግ/ፋ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች (ህጋዊ) ወኪሎቻቸው በተገኘበት ጨረታው በጋዜጣ በወጣበት በ11ኛው የሥራ ቀን ጠዋት 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ ጠዋት 4፡30 ላይ በት/ቤቱ በግ/ፋ/ን/አስ/ ቡድን ቢሮ ቁጥር 4 ይከፈታል።
- ት/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ካዛንችስ ቶታል ፊት ለፊት ወደ አዋሬ መሄጃ መንገድ ምስ/ጎህ/2ኛ ደረጃ ት/ቤት
ስልክ ቁጥር 0115-15-56-52
ምስራቅ ጎህ አጠቃላይ 2ተኛ ደረጃ ት/ቤት